እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር የ2014 ዓመተ ምህረቱ የUnited States የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ግምገማ፣ በዓለም ላይ የአሸባሪ ቡድኖችን መነሳት፥ የግጭቶች መጨመር፥ ሙስናና የመጥፎ አስተዳደር መንሰራፋት የደቀኑት ችግሮች ላይ ያተኩራል።
እራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራዉ አይነት ነዉጠኛ ቡድን መነሳሳት፣ እንደ ግብጽ ያሉ መንግስታት ተቃዋሚዎቻቸዉ ላይ ጥብቅ የቁጥጥር እርምጃ መዉሰድ እናም በምስራቃዊ ዩክሬን የሚካሄደዉ ዓይነት የእርስ በርስ ግጭት በያለበት መከሰት 2014 ን የሰብአዊ መብት ያዘቀጠበት ዓመት አሰኚቷል ብለዋል ዘገባዉን ይፋ ያደረጉት የUnited States ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር John Kerry
ሪፓርቱ አሰቃቂ ወንጀሎችን በመፈጸም እስላማዊ መንግስትና ሌሎች አክራቢ ቡድኖችን ይከሳል። በኢራቅና በሶሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀልና ሰብአዊ ቀዉስ በመፍጠር ይኮንናቸዋል።
በአፍሪቃ እንደ አልሸባብና ቦኮ ሃራም ላሉ ቡድኖች መፈጠር ምክንያቱ የባለስልጣናት በስልጣን መባለግና መጥፎ አስተዳደር መሆኑን በሪፓርቱ ተመልክቷል።
በአዉሮፓ፣ ሩሲያ በመገናኛ ብዙሃን በሲቪል ማህበረሰቡና በሚቃወሙዋት ዜጎች ላይ ቁጥጥርዋን እንዳጠበቅች፥ በኢስያ፣ ቻይናና ታይላንድ የሲቪል መብትን እንደሚረግጡ ፥ በላቲን አሜሪካ ቬንዚዌላ ባለስልጣናትን የሚተቹትን እንደምታስርና እንደምታዋክብ ተጠቅሷል።
እንደ ኢትዮጵያ፣ ኤርትርራ ኢራን እና ሳኡዲ አረቢያ ያሉ መንግስታት ደግሞ ጋዜጠኞችን ጦማሪያንና በሰላማዊ መንገድ ሂስ የሚሰነዝሩባቸዉ ዜጎችን እንደሚያሳድዱ አመታዊዉ የአሜሪካ የሰብአዊ መብት ዘግቧል።
ዝርዝሩን ያዳምጡ።