ኢትዮጵያን፣ ሶማሊያን እና ኬኒያን ጨምሮ በዓለም አቀፍ የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ቀውስ ክፉኛ በተጎዱ 12 ሀገሮች ካለፉት አራት ዓመታት ጅምሮ በተለይ በከባድ የምግብ እጥረት የተጎዱ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች እንዲሁም ታዳጊ ልጃገረዶች ቁጥር ማሻቀቡ ተገለጸ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ ባለፈው ሳምንት ባወጣው አዲስ ሪፖርት እንዳስታወቀው አሃዙ ከ5.5 ሚልዮን ወደ 6.9 ሚልዮን በማደግ 25 ከመቶ ጨምሯል፡፡
ዘገባውን ከተያያዘው ፍይል ይከታተሉ።