ዋሽንግተን —
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዛይድ ራዓድ አልሁሴን ኢትዮጵያ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፎች በተካሄዱባቸው አካባቢዎች ዓለምአቀፍ ታዛቢዎች ገብተው እንዲመለከቱ መንግሥት እንዲፈቅድ ጥሪ አቅርበዋል።
ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ሂዩማን ራይትስ ዋች ደግሞ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩት ዕጩዎች በአሜሪካና በተቀረውም ዓለም ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማድረግ ያላቸውን አቋም ግልፅ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ተወዳዳሪዎቹ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ ዋና ዋና የሚባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥያቄዎችን እንዴት እንደሚመለከቱ ለማወቅ የመብቶች ተሟጋቹ ቡድን 12 ጥያቄዎችን አቅርቧል።
“ሰብዓዊ መብቶችን ከሚረግጡት ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት” ብሏል ሂዩማን ራይትስ ዎች።