በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለኢትዮጵያ ተፈናቃዮች ዩኤንኤችሲአር አፋጣኝ እርዳታ ጠየቀ


የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር

በደቡብና በኦሮምያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በሚኖሩ ማኅበረሰቦች መካከል ካለፈው ሚያዝያ ወዲህ በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ ሲቪሎች ለመፈናቀል መገደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር አስታውቋል።

በደቡብና በኦሮምያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በሚኖሩ ማኅበረሰቦች መካከል ካለፈው ሚያዝያ ወዲህ በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ ሲቪሎች ለመፈናቀል መገደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር አስታውቋል።

ግጭቶቹ የተስተዋሉት ከአንድ ዓመት በላይ ከዘለቀ ድርቅ በኋላ በተለያዩ የተፈጥሮ ኃብት ዙሪያ በተነሱ ውጥረቶች መሆኑንም ዩኤንኤችሲአር አክሎ ጠቁሟል።

ባባር ባሎች - የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር /ዩኤንኤችሲአር/ ቃል አቀባይ
ባባር ባሎች - የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር /ዩኤንኤችሲአር/ ቃል አቀባይ

ቤቶቻቸው እፊታቸው ላይ የተቃጠሉባቸውና የወደሙባቸው፣ ጎረቤቶቻቸው ለጥቃት የተነሱባቸው ሰላማዊ ሰዎች እላይቸው ላይ ካጠለቁት ልብስ በስተቀር የተረፋቸው፣ የያዙትም አንዳች ጥሪት ሳይኖር ለመሸሽ እንደተገደዱ መናገራቸውን የዩኤንኤችሲአር ቃል አቀባይ ባባር ባሎች ጄኔቫ ላይ ዛሬ የሰጡትን መግለጫ ጠቅሳ ሪፖርተራችን ማርጋሬት በሽር ዘግባለች።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባቀረበለት ጥያቄ መሠረት የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ተቋም ለፈተናቃዮቹ አፋጣኝ ፍላጎቶች ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ያመለከቱት ባሎች ኮሚሽነሩ በጌዴዖና በምዕራብ ጉጂ አካባቢዎች ሁለት የአፋጣኝ እርዳታ ሰጭ ቡድኖችን አሠማርቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቀዋል።

ምንም እንኳ ሰዎች አሁንም እየተፈናቀሉና እየሸሹ መሆናቸውን ቢቀጥሉም ወደ ሁለት መቶ ሺህ የሚሆኑ ወደ ቀድሞ መኖሪያ አካባቢዎቻቸው መመለሳቸውን መንግሥቱ መግለፁን ባባር ባሎች አመልክተዋል።

ሰዎች ወደየቀድሞ ቀያቸውና መኖሪያቸው ሲመለሱ በራሳቸው ፍቃድ ብቻ እንዲሆን፣ ሰብዓዊ ክብራቸውም እንደተጠበቀ መሆኑ እንዲረጋገጥ ዩኤንኤችሲአር እና ሌሎችም አጋሮች አሳስበዋል።

በመመለሱ ጉዳይ ላይ የተለያዩ አመለካከቶች ቢኖሩም በአካባቢዎቹ ሁከት ሊያገረሽ ይችላል በሚል ሥጋት ለመመለስ እያመነቱ ያሉ ሰዎችም መኖራቸውን የዩኤንኤችሲአር ቃል አቀባይ መግለጫ ይጠቁማል።

ከተፈናቀሉት ብዙዎቹ የተጠለሉት በትምህር ቤቶች በሆስፒታሎችና በሌሎችም የመንግሥትና የሕዝብ ተቋማት ውስጥ መሆኑንም እዚያው የሚገኙት የዩኤንኤችሲአር ቡድኖች ገልፀዋል።

ወደየቀድሞ ቤታቸውና ወደየእርሻቸው ወይም ማሳቸው የተመለሱ ሰዎች ሲደርሱ ትምህርት ቤቶች፣ የቡና ማምረቻና ማደራጃዎች፣ የጤና ጣቢያዎችና ሌሎችም የመሠረተ-ልማት ተቋሞች ወድመው ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ተፈናቃዮችም ሆኑ ተፈናቃዮቹን እያስተናገዱ ያሉት ማኅበረሰቦች እራሳቸውም የምግብ፣ የውኃ፣ የብርድ ልብስ፣ የማብሰያ ግብዓቶችና የመሳሰሉ መሠረታዊ አቅርቦቶች የበረታ ችግር እንዳለባቸው ዩኤንኤችሲአር አስታውቆ በአካባቢው የወቅቱ የከበደ ዝናብ ከመጀመሩ በፊት የመጠለያ ቁሳቁስ፣ የላስቲክ ሽፋንና ሌሎችም አቅርቦቶች በአፋጠኝ ሊደርሱላቸው እንደሚገባ አሳብቧል።

ለመጭዎቹ 12 ወራት አፋጣኝ እርዳታ ለማድረስ እንዲቻል የ21.5 ሚሊዮን ዶላር አጣዳፊ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ኮሚሽነሩ አስታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG