በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶሪያ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ተመድ ጠየቀ


አንቶንዮ ጉቴሬዥ
አንቶንዮ ጉቴሬዥ

ሰሜን ምስራቃዊ ሶሪያ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ አሳሰቡ።

በባለፈው ሳምንት የሃገሪቱ መንግሥት በአካባቢው በከፈተው ጥቃት በብዙ አስር ሺዎች የተቆጠረ ህዝብ ከመኖሪያው ተፈናቅሏል።

ዋና ጸኃፊ ጉቴሬዥ የተከፈተው ወታደራዊ ጥቃት ግዙፍነት እና ሲቪሎ ች መኖሪያቸውን እየጣሉ ወደሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የሚሸሹበትንም መስመርም እየደበደቡ ነው የሚሉት ዘገባዎች ዋና ጸኃፊውን እንዳሳሰቡዋቸው ትናንት ቃል አቀባያችው ያወጡት መግለጫ አመልክቷል።

የሶሪያ መንግሥት የርስ በርስ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት እኤአ ከ2011 ወዲህ ሽምቅ ተዋጊዎች ከያዝዋቸው ግዛቶች አሁንም በነሱ እጅ ያለች የመጨረሻዋ የሆነችውን ኢድሊብን ለማስለቀቅ እየሞከረ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG