በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሌራ ወረርሽኝ በየመን


ፎቶ ፋይል፡-የኮሌራ ወረርሽኝ በየመን
ፎቶ ፋይል፡-የኮሌራ ወረርሽኝ በየመን

ከባድ የገንዘብ እጥረት ስላለ የየመኑ የኮሌራ ወረርሽኝ እየተባባሰ ነው ሲል የተባብሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት በየመን ከአራት መቶ ስልሳ ሺህ በላይ በበሽታው ተይዘዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች እንዳሉ እና ሰባት መቶ አምስት ሰዎች መሞታቸውን የዋና ፀኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ ቃል አቀባይ ገልፀዋል። ባለፈው ዓመት በንፅፅሩ ተጠርጣሪ የበሽታው ተያዦች ሦስት መቶ ሰማኒያ፣ የሞቱት ደግሞ ሰባ እንደነበሩ ጠቅሰዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የየየመን ሰብዓዊ ረድዔት ምላሽ ዕቅድ ቃል አቀባዩ የኮሌራ ተያዦችን ለመርዳት አራት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልፀው፣ እስካሁን የገባው ግን ሠላሳ ሁለት ከመቶው ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG