የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የተዘጋው እአአ በ1991 ሶማልያ ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነት ይካሄድ በነበረበት ወቅት ነው።
አዲሱ ኤምባሲ ያወጣው መግለጫ ሞቃዲሾ ውስጥ መልሶ ኤምባሲ የማቋቋሙ ተግባር የቀጠለው የዩናይትድ ስቴትሳና የሶማልያ ግንኙነት ተጨማሪ ዕርንጃ መራመዱን ያሳያል ይላል።
በሶማልያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ዶናልድ ያማምቶ የኤምባሲው መልሶ መቋቋም ሶማልያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ያሳየችውን መሻሻል በጉልህ የሚያንፀባርቅ ታሪካዎ ቀን ነው ሲሉ ገልፀዋታል። ኤምባሲው ትብብርን የጠነክራል፣ የዩናይትድ ስቴትስን ስትራቴጃዊ ጥቅም ያራምንዳል፣ የፀጥታ ደኅንነታችንን፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ ልማት ግብንና ዓላማን ይረዳል ሲሉም አምባሳደሩ አክለዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ካለፈው ታህሳስ ወር አንስታ ሞቃዲሾ ውስጥ ዲፕሎማስያዊ ሚስዮን ነበራት።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ