በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ም/ቤት በሞስኮ ጥያቄ በባዮሎጂካል የጦር መሳሪያዎች ጉዳይ እየተነጋገረ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በሩሲያ እና በዩክሬን ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ዋና መሥሪያ ቤት ሲወያዩ፤ ኒው ዮርክ፤ እአአ ጥር 31/2022
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በሩሲያ እና በዩክሬን ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ዋና መሥሪያ ቤት ሲወያዩ፤ ኒው ዮርክ፤ እአአ ጥር 31/2022

የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት "ዩክሬን የኬሚካል ጦር መሳሪያ ሰርታለች” ስትል ሞስኮ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት ነው የተሰበሰበው።

ሩሲያ ትናንት ሐሙስ ባቀረበችው በዚህ ክሷ ዩክሬን ለምትሰራው የኬሚካል የጦር መሣሪያ የምርምር ሥራ ዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ድጋፍ ታደርጋለች ስትልም ጨምራ ከሳለች።

ዋሽንግተን እና ኪየቭ ውንጀላውን አስተባብለዋል። ዩናይትድ ስቴትስ በተጨማሪም ሞስኮ ይህን ዓይነት የጦር መሳሪያ በቅርቡ ልትጠቀም እንደምትችል ማሳያ ነው” ስትል ተናግራለች።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው በትናንትናው ዕለት ባሰሙት እና በቪዲዮ አማካኘት በተሰራጨ ንግግራቸው “ዩክሬን ውስጥ ማንም ጅምላ ጨራሽ የሆኑ የኬሚካልም ሆነ ሌላ ማንኛውንም መሳሪያ እየሰራ አይደለም” ሲሉ የሩሲያን ውንጀላ ውድቅ አድርገዋል።

ምዕራባውያን አገሮች የፖለቲካ ተቀናቃኞችን በመርዝ በመጉዳት ሩሲያን ይወነጅላሉ።

በሌላ ዜና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባትይ ኔድ ፕራይስ፣ ሩሲያ በዩክሬን የኬሚካል ጦር መሳሪያ እንዳትጠቀም እና ሲቪሎችን ኢላማ እንዳታደርግ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

"ይህ ከዚህ ቀደም የተከለከለውን የኬሚካል ጦር መሳሪያ በገዛ ህዝቡ ላይ የተጠቀመ መንግሥት ነው። በሩሲያ ግዛት ውስጥ ተጠቅመውታል። እንግሊዝ ውስጥም እንዲሁ። በገዛ ህዝቡ ላይ የተከለከሉ ኬሚካላል መሳሪያዎችን የተጠቀመውን ጨካኙን የአሳድን መንግሥትም ደግፈዋል።

በመሆኑም ይህ መንግሥት ምን ዐይነት መንገዶችን ሊጠቀም እንደሚችል .. ከዚህ ቀደም ምን ዓይነት መንገዶችን ተጠቅሞ እንደነበር እናውቃለን። ሌላው የሚያሳስብን ጉዳይ ግን ስለ ክሬምሊን ስልቶች የምናውቀው ነገር ነው። በተለይም የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት የማወናበድ ስልቶቹ።" ነበር ያሉት።

የመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በአሁኑ ወቅት በዚህ እና በአጠቃላይ በዩክሬን ጉዳይ በመነጋገር ላይ ነው።

XS
SM
MD
LG