በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ጥሪ፡ ለሁሉም ወገኖች


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ “የኢትዮጵያ ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ የሚያሳስባቸው መሆኑን በመግለጽ “ አሁን ሁሉም ወገኖች ችግሩ ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው መገንዘብ ያለባቸው ጊዜ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው ይህን የተናገሩት ትናንት የተከበረውን የዓለም የሰብአዊነት ቀን ምክንያት በማድረግ ነው፡፡

ጉቴሬዥ “በተለየ ሁኔታ ያሳስበኛል” ላሉት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ ሶስት የመፍትሄ ሀሳቦችን በመሰንዘር ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

“ዛሬ የዓለም የሰብአዊነት ቀን ነው፡፡ የሰአብዊ እርዳታ የሚሹ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በየእለቱ የሚረዱ የሰአብዊ እርዳታ አገልግሎት ሰጭዎችን እናስባቸዋለን፡፡” ያሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጎተሬዥ ናቸው፡፡

እንደ ሄይቲ እና አፍጋኒስታን ያሉትን የህይወት አድን ሠራተኞች ተግባራትን ያወሱት ዋና ጸሀፊው ፣ ኢትዮጵያንም በተለየ መንገድ አንስተዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ጥሪ፡ ለሁሉም ወገኖች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:39 0:00


“የዓለም የሰብአዊነት ቀን በሚከበርበት በዚህ እለት በተለይ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ያሳስበኛል” ብለዋል ፡፡

"የኢትዮጵያ ህዝብ ብዙ ጉዳት ደርሶበታል፡፡" ያሉት የሰብአዊነት ሁኔታዎች የገሀነም ያህል ሆነዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እርዳታ ይሻሉ፡፡ የመሠረተ ልማቶች ወድመዋል፡፡ የማይነገር የጥቃት ዓይነት የደረሰባቸው ሴቶች መኖራቸውን ከራሳቸው አንደበት ሰምተናል፡፡ የተስፋፋው ግጭት በርካታ ተጨማሪ ሰዎች ወደ በለጠው ሰቆቃ እንዲገቡ አድርጓቸዋል፡፡ አሁን ሁሉም ወገኖች ችግሩ ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው መገንዘብ ያለባቸው ጊዜ ነው፡፡ የኢትዮጵያን አንድነትና መረጋጋት መጠበቅ ለኢትዮጵያ፣ ለቀጠናውም ከዚያም አልፎ ላለው ሁሉ አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡” በማለት ጉተሬዥ ተናግረዋል፡፡

“ይህን ሰቆቃ ለማስወገድ ጊዜው አሁን ነው፡፡” ያሉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ፣ በኢትዮጵያ ላለው ችግር ለሰላም እድል ለመስጠት ወሳኝ ናቸው ያሏቸውን፣ ሶስት ነገሮች ተግባራዊ እንዲደረጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

“አንደኛ ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ግጭቱን እንዲያቆሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡”

ሁለተኛ በሁሉም አካባቢዎች የህዝባዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ በሁሉም አካባቢዎች ያልተገደበ ሰብአዊ ተደራሽነት እንዲኖር ዋስትና እንዲሰጥ

ሶስተኛ ለቀውሱ መፍትሄ የሚሻ፣ ኢትዮጵያ መር የሆነ ብሄራዊ የፖለቲካ ውይይት እንዲኖር ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ” በማለት መንገዶቹን ዘርዝረዋል፡፡

አያይዘውም "እንደዚያ ያሉ ንግግሮች የግጭቱን መሠረታዊ ምክንያቶች ለማወቅና የኢትዮጵያውያን ድምጾች በቀጥታ እንዲደመጡ በማድረግ፣ ወደ ሰላም የሚያመራ ጥርጊያ መንገድ ይከፍታሉ፡፡” ብለዋል፡፡

ሁለቱም ወገኖች የግጭቱን ማቆም አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ ለማሳመን የታቸለንን አድርገናል፡፡” ያሉት ጉተሬዥ፣ “ይህንንም ለማሳሰብ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ብዙ ጊዜ ተገናኝቻለሁ፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ልዩ መልክተኛቸው ማርቲን ግሪፍትስመገናኘት ከሚችሉት ጋርና እንዲሁም ከዶ/ር ደብረጽዮን ጋርም እንዲገናኙ የነገሯቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ ሰላምና እርቅ የሚወስደውን መንገድ እንዲይዝ ፣የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ከአፍሪካ ህብረት ጋር፣ እንዲሁም ከአካባቢው አገሮች እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመሆን መስራቱን ይቀጥላል፡፡” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ዋና ጸሀፊው፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጨምሮ በአካባቢው ካሉ በርካታ አገሮች ጋር እየተነጋገሩበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

“ሁሉም አገሮች የኢትዮጵያን አንድነትና መረጋጋት መጠበቅ እንደሚገባ ይህ ግጭት መቆም እንዳለበት የሚያምኑ መሆኑን አስተውያለሁ፡፡” ብለዋል፡፡

ከዓለም አቀፉ ማህበረብሰም ጋር ጉዳዩን በተነሳሽነት ይዘው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ወገኖች መኖራቸውንም ሲያስረዱ የሚከተለውን ተናግረዋል፡፡

“ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት ተነሳስተው ከሚንቀሳቀሱ ሌሎች አካላትም ጋር በቅርብ እየተገናኘሁ ነው፡፡ እንድምታውቁት በአሜሪካ በኩል የሚደረግም የተነሳሽነት ጥረት አለ፡፡ ስለዚህ ሁላችንም ወደ ተመሳሳይ አቅጣጫ እየገፋነው ነው፡፡ ለተባበሩት መንግሥታ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በትናንትናው እለት ማብራሪያ ሰጥቻለሁ፡፡ እኔና የጸጥታው ምርክቤትም ጋር በሚቀጥለው ሳምንት እንደገና እንገኛለን፡፡ ይህ ያቀረብኩት ማሳሳቢያ በመላው ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት እንደሚኖረው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡”

የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነትንም በተመለከተ፣ በትግራይእናበአካባቢው ባሉ ክልሎች፣ በአሁን ሰዓት ብርቱ ችግር የደረሰባቸው ሰዎች መኖራቸውን በመጥቀስ በዚሁ እለት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር መነጋገራቸውን አመልክተዋል፡፡

“ሁሉም ተሳታፊ ወገኖች በተለይ የኢትዮጵያ መንግሥትን በአካባቢው የሰአብአዊ መብት ተደራሽነት እንዲኖር ሙሉ ለሙሉ ክፍት እንዲደረግ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ዛሬ ጧት ራሱ በድጋሚ በዚህ ጉዳይ ላይ አነጋግሬያቸዋለሁ፡፡” ብለዋል፡፡

ሁለቱም ወገኖች ግጭቱ እንዲቆም የቀረበውን ጥሪ መቀበል አለባቸው፡፡ የተቋረጠውን ህዝባዊ አገልግሎት እንደገና መጀመርና በሁሉም አካባቢዎች በተለይ በትግራይ በአፋር እና በአማራ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነት ሙሉ ለሙሉ መክፈት ፍጹም አስፈላጊ መሆኑን ሁሉም ሰው መረዳት ይኖርበታል፡፡

በእስካሁን ንግግሮቻችሁም ሆነ ጥያቄዎቻቸሁ ከሁለቱም ወገኖች የምታገኟቸው ምላሾች ምንድናቸው የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፡፡

ዋና ጸሀፊው ነገሮች እንደሚሻሻሉ ቁርጠኝነቱ እንደነበር ገልጸው “ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ግን የሚሆነውን እናያለን፡፡” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG