በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ - የጦርና የስብዓዊ ወንጀሎችን የፈፀሙ የደቡብ ሱዳንን ባለሥልጣናት ማወቁን ገለፀ


ፎቶ ፋይል፡-የደቡብ ሱዳን ወታደሮች
ፎቶ ፋይል፡-የደቡብ ሱዳን ወታደሮች

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪዎች ከ40 በላይ የሚሆኑ የጦርና የሰብዓዊ ወንጀሎችን በመፈፀም ኃላፊነት እንዳለባቸው የሚታመኑ ከ40 በላይ የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናትና ወታደራዊ መኮንኖችን ማንነት አውቀናል ብለዋል።.

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪዎች ከ40 በላይ የሚሆኑ የጦርና የሰብዓዊ ወንጀሎችን በመፈፀም ኃላፊነት እንዳለባቸው የሚታመኑ ከ40 በላይ የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናትና ወታደራዊ መኮንኖችን ማንነት አውቀናል ብለዋል።.

የተጠቀሱት ወንጀሎች የተፈፀሙት በ10 ሺሕዎች በተገደሉበትና ከ4 ሚሊዮን በላይ ሌሎች በተፈናቀሉበት ሀገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የርስ በርስ ጦርነት ወቅት ነው።

ዛሬ በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ይፋ የተደረገው ሪፖርት፣ በሲቪሎች ላይ የተፈፀሙ አሰቃቂ እና አረመኔዊ ድርጊቶችን ይዘረዝራል። የአንዳንዶቹ የጥቃቱ ሰለባዎች ዓይን ፈሷል፣ እንደ ከብት ታርደዋል፣ ተኮላሽተዋል ወይም ተሰልበዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ በኃይልና በብዛት ወሲብ የተፈፀምባቸው ሲሆን ድርጊቱን የቤተሰብ አባላት እንዲመለከቱ መድረጋቸውንም ሪፖርቱ ጨምሮ አጋልጧል።

ሪፖርቱ በተጨማሪም የመርማሪው ኮሚሽን አባል አድንሪው ክላፕሃም በሰብዓዊ ወንጀሎች ሊከሰሱ በሚገባቸው - በአብዛኛው የመንግሥት ኃይሎች በግልፅ የተፈጸሙ ዘር ተኮር ጥቃቶች ሲሉ የገለጿቸው ድርጊቶችንም ዘርዝሯል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪዎች፣ ይህን የዛሬውን ሪፖርት ያወጡት፣ 230 ዕማኞች የሰጧቸውን መግለጫዎችና ከ60 ሺሕ በላይ ሰነዶችን መሠረት በማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።

ደቡብ ሱዳን ውስጥ እአአ በ2013 ዓ.ም የርስ በርስ ጦርነቱ የፈነዳው በአብዛኛው የፕሬዚዳንት ሣልቫ ኪር ደጋፊ በሆኑት የዲንቃ ብሄረሰብ አባላትና በቀድሞ ምክትላቸው በሪክ ማቻር ሽምቅ ተዋጊ ኑዌሮች መካከል ግጭት በመፈጠሩ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል።

በሪፖርቱ መሠረት በሚሥጥር የተያዘው የ41 ተጠርጣሪዎች ስም ዝርዝር - በተባበሩት መንግሥታት ለሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ለዛይድ ራዳ አልሁሴን ተልኳል።

ከሚጠረጠሩት ውስጥም፣ ሦስቱ የክፍለ ግዛት አስተዳዳሪዎች 33ቱ ጄነራሎችና 5ኮሎኔሎች ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG