በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሊቢያ የሚነሱ መርከቦች ፍተሻ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ተመድ ወሰነ


ከሊቢያ የሚነሱ መርከቦች ፍተሻ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ተመድ ወሰነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:46 0:00

ከሊቢያ የሚነሱ መርከቦች ፍተሻ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ተመድ ወሰነ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ከሊቢያ ባህር ዳርቻ በሚነሱና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ በማስተላለፍ በሚጠረጠሩ መርከቦች ላይ የሚደረገው ምርመራ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም በአንድ ድምጽ ወስኗል።

ም/ቤቱ ትናንት፤ ሐሙስ ያስተላለፈው የውሳኔ ሃሳብ በሜድትሬንያን ባህር ላይ የሚካሄደውን ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ለማስቆም የሚደረገው ጥረት በተጠናከረ መንገድ መቀጠሉን ያሳያል ተብሏል።

የተመድ ዋና ጸሃፊ የሆኑት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በቅርብ በወጣ ሪፖርት ላይ እንዳስቀመጡት፣ የሜዲትሬኒያን ባህር “ወደ አውሮፓ ለመሻገር ለሚሞክሩ ፍልሰተኞችና ስደተኞች አደገኛ የሞት መንገድ ከሆኑት መሻገሪያዎች አንዱ ነው” ብለዋል። ከሊቢያ የሚነሱ ፍልሰተኞችን እንደገና የማስፈር ጉዳይ ይበልጥ እንዲጠናከርም አሳስበዋል።

የጸጥታው ም/ቤትም ትናንት ባደረገው ስብሰባ ከሊቢያ ባህር ዳርቻ በሚነሱና ሰዎችን በህገወጥ መንገድ በማስተላለፍ በሚጠረጠሩ መርከቦች ላይ የሚደረገው ምርመራ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም በአንድ ድምጽ ወስኗል።

ውሳኔው “ወደ ሊቢያ፣ በሊቢያ በኩል እና ከሊቢያና የባህር ዳርቻዎቿ የሚደረጉ ማንኛቸውንም ዓይነት ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን አውግዟል። ሊቢያን ለማረጋጋት የሚደረገውን ጥረት የሚጎዳና፤ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወትንም አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ተብሏል።

በሊቢያ የረጅም ዘመን መሪ የነበሩት ሞአመር ጋዳፊ ከ 11 ዓመታት በፊት በአመጽ ከስልጣን ተወግደው ከተገደሉ በኋላ፣ ሃገሪቱ ወደ ለየለት ትርምስ ስትገባ፤ ጦርነትንና ድህነትን ለማምለጥ ከአፍሪካና ከአውሮፓ ለሚነሱ ፍልሰተኞች መተላለፊያ ሆናለች።

አብዛኞቹ ፍልሰተኞች አደገኛውን ጉዞ የሚያደርጉት እንደነገሩ በተሰራ የጎማ ጀልባ ላይ ነው።

በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች የሜድትሬንያን ባሀርን ለማቋረጥ እየሞከሩ ባለበት ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት “የሶፊያ ዘመቻ” ብሎ የሰየመውን በባህር ላይ ህይወት የማዳን ተልዕኮ በእ.አ.አ 2015 ቢጀምርም፤ “የጦር መርከቡ ጭራሽ ተጨማሪ ስደተኞች ወደ አውሮፓ እየሳበ ነው” በሚል ጣሊያን ተልዕኮውን አግዳለች።

ትናንት በተሰራጨው የተመድ ዋና ጸሃፊ ሪፖርት መሠረት፣ እስካለፈው ነሀሴ ወረ ድረስ፣ 1 ሺህ 751 ስደተኞችና ፍልሰተኞች በሜድትሬኒያን ባሀር ላይ ህይወታቸውን አጥተዋል ወይም የደረሱበት አልታወቀም ሲሉ የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮና ዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት ግምታቸውን እንዳስቀመጡ ተመልክቷል። ሆኖም ቁጥሩ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ 2 ሺህ 192 ቀንሷል።

የአውሮፓ ኅብረት በበኩሉ፣ 52ሺህ 537 ስደተኞችና ፍልሰተኞችን ከሊቢያ በህር ዳርቻዎች አካባቢ ለማዳን መቻሉን አስታውቋል። ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ካዳነ በኋላ መልሶ ወደ ሊቢያ ልኳል።

ጉቴሬዝ እንዳሉት “ፍልሰተኞችን ደብቆ በህገወጥ መንገድ ማስተላለፍ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ህግጋትን የሚተላለፍ ተግባር ነው። በጅምላ ሰዎችን ከአንድ ሀገር ማስወጣትም በዓለም አቀፍ ሕግ የተከለከለ በመሆኑ መቆም አለበት።”

ዋና ጸሃፊው በተጨማሪም፣ ወደ ሊቢያ በህገወጥ መንገድ በሚያመሩ መስመሮች ላይ ያሉ ሃገራት ከችግሩ የተረፉ ሰዎችን እንዲንከባከቡና፣ ድርጊቱንም ሕገ-ወጥ አድርገው እንዲኮንኑ መክረዋል።

ሃያ ሰባቱም የአውሮፓ ኅብረት ዓባል ሀገራት “የሚስማሙበትና በጋራ ሃላፊነትን የሚወስዱበት፣ ፍልሰተኞችንና ስደተኞችን ለመቀበል ያለመ የትብብር ስምምነት እንዲደረግ” ዋና ጸሃፊው ጉቴሬዝ በድጋሚ ጥሪ አድርገዋል።

“ከአደጋ ነጻ የሆነና፣ ለሕጋዊና መደበኛ ፍልሰተኞች የሚውል፣ ለሰው ሕይወት ክብር የሚሰጥ መተላለፊያ እንዲስፋፋና፤ የሕገወጥ ፍልሰተኞችን በተመለከተ ደግሞ የችግሩን ምንጭ ለማሰወገድ ሁሉን አቀፍ መፍትሄ መሻት አስፈላጊ መሆኑን” ዋና ጸሃፊው አስምረውበታል።

XS
SM
MD
LG