No media source currently available
በድርቅ የተጎዱ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን ቀደም ሲል ከተገመተው በላይ መጨመሩን፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታውቋል። በዚህም መሠረት፥ የሚያስፈልገው ገንዘብ ከአንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ከፍ ማለቱን ይፋ አድርጓል።