በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከየመን ከአምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች መሰደዳቸውን ተመድ ገለፀ

ከየመንዋ የወደብ ከተማ ከሁዴይዳ እና ዙሪያዋን ካሉት አካባቢዎች ውጊያውን ሸሽተው ከአምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

ከየመንዋ የወደብ ከተማ ከሁዴይዳ እና ዙሪያዋን ካሉት አካባቢዎች ውጊያውን ሸሽተው ከአምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

ውጊያው በመቀጠሉም የሚሰደደው ህዝብ ቁጥር ይጨምራል ብለን እንጠብቃለን ሲሉ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ ገልጠፀዋል።

አሁንም ሆዴይዳ ውስጥ ቁጥራቸው ወደስድስት ሺህ የሚጠጉ ሲቪሎች እንዳሉ የጠቆሙት የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅቶች ምግብ ነዳጅ እና የአጣዳፊ ዕርዳታ ጥቅሎችን አዘጋጅተዋል ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG