በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በሶማሊያ ቦሳሶ ወደብ


ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በሶማሊያ ቦሳሶ ወደብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:59 0:00

ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከሶማሊያ ቦሳሶ ወደብ ተነስተው ቀይ ባህርን በጀልባ ለመሻገር ሲሞክሩ ይሞታሉ፡፡ የሶማሊያ ፑንትላንድ ባለሥልጣናት እንደሚገልፁት ከኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች በመነሳት ፍልሰተኞቹ ባህርና በረሃ አቋርጠው የሶማሊያ ወደብ በሆነችው ቦሳሶ ለቀናት ይከትማሉ፡፡

እንደ ዓለማቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት /አይኦኤም/ ዘገባ አደገኛውን የበረሃ ጉዞ ሲያቋርጡ በውሃ ጥምና ርሃብ በድካም የሚሞቱ አሉ፡፡ በሴቶች ላይ የሚፈፀመው የወሲብ ጥቃትና የፆታ ሁከት የተለመዱ ናቸው።

ከበርሃው የተረፉት ቀይ ባህርን በጀልባ ለማቋረጥ በሚያደርጉት ጎዞም የመስጠም አደጋ እንደሚደርስባቸው ይታወቃል፡፡

እነዚሁ ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚነሱት ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች፣ ህልማቸው ቀይ ባህርን ተሻግረው የመን መድረስ ሲሆን ከዚያም ወደ ሳዕዲ አረቢያና ሌሎች የአርብ ሀገራት መዝለቅ ነው፡፡

በሶማሊያ የፑንትላንድ የንግድ ከተማ ቦሳሶ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተታለው፣ ለአደገኛው የባህር ጉዞ ለቀናት በከተማዋ ቆይታ የሚያደርጉት ፍልሰተኞች ቁጥር መጨመሩን አለማቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት /አይኦኤም/ ገልጿል፡፡

አለማቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት /አይኦኤም/አደገኛውን የባህር ጉዞ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የነበሩ ከአርባ በላይ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን በያዝነው ሳምንትም ወደ እየመጡበት ክልል መልሷል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG