በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር በኢትዮጵያ

ፎቶ ፉይል:-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራ’አድ አል ሁሴን
ፎቶ ፉይል:-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራ’አድ አል ሁሴን

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራ’አድ አል ሁሴን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ጉዳዮች ላይ ከመንግሥት ባለሥልጣናትና ከተቃዋሚዎች መሪዎች ጋር ለመነጋገር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራ’አድ አል ሁሴን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ጉዳዮች ላይ ከመንግሥት ባለሥልጣናትና ከተቃዋሚዎች መሪዎች ጋር ለመነጋገር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ከፍተኛ ኮሚሽነሩ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙት በኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ መሆኑን መሥሪያ ቤታቸው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ሚስተር ራ’አድ አል ሁሴን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፣ ከፓርላማው አፈጉባዔ፣ ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም በቅርቡ ከእሥር ከተፈቱ የመንግሥቱ ተቺዎችና ሌሎችም ጋር እንደሚገናኙ ታውቋል።

ከፍተኛ ኮሚሽነር ራ’አድ አል ሁሴን ለአራት ቀናት ጉብኝት ኢትዮጵያ የገቡት ትናንት ሲሆን ነገ፤ ማክሰኞ በአፍሪካ ኅብረትና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች የከፍተኛ ደረጃ ጥምር ውይይት ላይ እንደሚገኙና ከውይይታቸው በኋላም ከኅብረቱ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር ሆነው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ታውቋል።

በከፍተኛ ኮሚሽነሩ የጉዞ መርኃግብር መሠረት ነገ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተገኝተው ሌክቸር እንደሚሰጡ ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG