በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በኢትዮጵያ ተፈናቃዮችን ጎበኙ


ፎቶ ፋይል፦ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛው ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በኡም ራኩባ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ
ፎቶ ፋይል፦ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛው ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በኡም ራኩባ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛው ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በኢትዮጵያ ስደተኞችን እና ተፈናቃዮችን ጎበኙ።

ከትናንት በስተያ ዕሁድ ኢትዮጵያ የገቡት የመንግሥታቱ ድርጅት ከፍተኛው ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ከኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲሆን ወደትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ተጉዘው በጦርነቱ ሳቢያ የተፈናቀሉ ቤተሰቦችን ጎብኝተዋል።

በአማራ ክልል ዓለምዋች የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ያሉ ኤርትራዊያን ስደተኞችንም ጎብኝተዋል።

ለሁለት ዓመታት በተካሄደው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ኤርትራዋያን ስደተኞች የተነጣጠረ ጥቃት ሲደርስባቸው የነበረ ሲሆን ባለፈው ታህሳስ ወር የተባበሩት መንግሥታት የስድተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ከሌሎች አጋሮቹ ጋር በመተባበር 7 ሽህ ኤርትራውያን ስደተኞችን ከምዕራብ ትግራይ ወደ አለምዋች ካምፕ ማዛወሩን ዘገባው አውስቷል።

የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ለማቆም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ የረደዔት ድርጅቶች በጦርነት ወደተጎዱት አካባቢዎች የበለጠ ዕርዳታ ለማጓጓዝ መቻላቸውን የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽነሩ ፊሊፖ ግራንዲ በትዊተር ባወጡት ቃል ተናግረዋል።

ወደትግራይ ክልል የሚገባው ዕርዳታ አቅርቦት የተሻሻለ ቢሆንም አሁንም ካለው ከባድ ችግር አንጻር በቂ አለመሆኑን አንድ የመንግሥታቱ ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG