በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ የተመድ ሄሊኮፕተር አል-ሻባብ በሚቆጣጠረው አካባቢ በድንገት ማረፉ ተነገረ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሄሊኮፕተር
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሄሊኮፕተር

አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሄሊኮፕተር አል-ሻባብ በሚቆጣጠረው ክልል ውስጥ ዛሬ በድንገት ማረፉን በርካታ የሶማሊያ ባልሥልጣናት ለቪኦኤ የሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት አስታውቀዋል።

በሄሊኮፕተሩ ውስጥ ያሉ ሰዎች ቁጥር በትክክል ባይታወቅም፣ የአል-ሻባብ ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር አውለዋቸዋል ብለው እንደሚያምኑ ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።

ሄሊኮፕተሯ ሂርሸበሌ ግዛት ከምትገኘው የበለደወይን ከተማ፣ ጋልሙዱግ ግዛት ወደምትገኘው ዊሲል ከተማ ለአጣዳፊ ሕክምና ጉዳይ አቅንታ እንደነበር ታውቋል።

“እክል ገጥሟት እንደነበርና አብራሪው ሊከተል የሚችለውን አደጋ ለማስቀረት ሲል ለማሣረፍ ወስኗል” መባሉን እንደሰሙ በጋልሙዱግ የሚገኙ ፋራ ዲሪዬ ዋርሳሜ የተባሉ ባለሥልጣን ለቪኦኤው ሃሩን ማሩፍ ተናግረዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ሌላ የሶማሊያ መንግስት ባለሥልጣንም፣ ሄሊኮፕተሩ ቴክኒካዊ እክል እንደገጠመው ተናግረዋል።

ሄሊኮፕተሩ ቲክኒካዊ እክል ይግጠመው ወይስ በአል-ሻባብ ተመትቶ ይረፍ ግልጽ አልሆነም።

በውስጡ የነበሩ የሰዎች ብዛትንም በተመለከተ፣ ዋርሳሜ ስድስት ይሆናሉ ሲሉ፣ አንድ ሌላ ባለሥልጣን ደግሞ ዘጠኝ ይሆናሉ ብለዋል።

የአል-ሻባብ ታጣቂች ሰዎቹን አግተው ሄሊኮፕተሯን እንዳቃጠሉ በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች እነደገሯቸው ዋርሳሜ ጨምረው ገልጸዋል።

በሶማሊያ የሚገኙ የተመድ ሄሊኮፕተሮች በዛች አገር ለሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት የሠላም ልዑክ፣ ለተመድ ቢሮ እና ለሶማሊያ መንግስት አገልግሎት እንደሚሰጡም ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG