No media source currently available
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ዛሬ ረቡዕ ለዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባላት ባሰሙት የቀጥታ ንግግር የሩሲያ ኃይሎች ላለፉት ሦስት ሳምንታት በሃገራቸው ላይ እያደረሱ ካሉት ጭፈጨፋ ለመከላከል ብዙ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡ በአሜሪካ ታሪክ ለረጅም ጊዜ ሆኖ የቆየውን ቁስል በመቀስቀስ ምክር ቤቱና ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የበለጠ ወታደራዊ እርዳታ እንዲሰጧቸው የዩክሬንን አየር ክልል ለበረራ የተከለከል ዞን በማድረግ እንዲወስኑ ጠይቀዋል፡፡