በዩጋንዳ ሁለተኛው የኢቦላ ታማሚ የአራት ዓመት ህፃን ህይወቱ ማለፉን የአለም ጤና ድርጅት፤ የሀገሪቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ገልጿል።
ሁኔታው በዩጋንዳ የተረጋገጠ የኢቦላ ሟቾችን አሃዝ አስር አድርሶታል።
በምሥራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር መዲና ካምፓላ ሙላጎ ብሔራዊ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የሚያገለግል አንድ ወንድ ነርስ ከሞተ በኋላ፤ ሀገሪቱ ባለፈው ጥር ወር በአደገኛ ሁኔታ ተላላፊ፣ ገዳይ እና ብዙ የደም መፍሰስ የሚያስከትል በሽታ መከሰቱን አስታውቃለች።
የዓለም ጤና ድርጅት የዩጋንዳ ጽህፈት ቤት ትላንት ቅዳሜ በኤክስ ማኅበራዊ ድረገጽ ላይ ዘግይቶ እንዳስታወቀው፤ ሚኒስትሩ ባለፈው ማክሰኞ “በሙላጎ ሆስፒታል ውስጥ የአራት ዓመት ተኩል ዓመት ሕፃን በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቱ አለፏል” ማለቱን ሪፖርት አድርጓል።
ሙላንጎ የኢቦላ ህክምና ሪፈራሎች የሚመጡበት በሀገሪቱ ያለ ብቸኛ ብሔራዊ ሆስፒታል ነው።
ሚኒስቴሩ በዚህ ዓመት በየካቲት ወር በእንክብካቤ ላይ ያሉ ስምንቱ የኢቦላ ታማሚዎች ታክመው ሲወጡ፤ በተጨማሪም 265 የሚሆኑና ከእነሱ ጋር ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦች በካምፓላ እና በሌሎች ሁለት ከተሞች ጥብቅ ማቆያ ውስጥ መቆየታቸውን አስታውቋል።
የኢቦላ ምልክቶች ትኩሳት፣ ራስ ምታት እና የጡንቻ ህመም ሲሆኑ፤ ቫይረሱ የሚተላለፈው ከተበከሉ የሰውነት ፈሳሾች እና አካላት ጋር በሚደረግ ንክኪ ነው።
መድረክ / ፎረም