በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአንድነት ሰልፎች በደሴና በጎንደር ተካሄዱ


ደሴ
ደሴ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መርኃግብሩ መሠረት ዛሬ በጎንደርና በደሴ ከተሞች ሠላማዊ ሰልፎችን አካሂዷል፡፡







አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ


please wait

No media source currently available

0:00 0:19:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መርኃግብሩ መሠረት ዛሬ በጎንደርና በደሴ ከተሞች ሠላማዊ ሰልፎችን አካሂዷል፡፡

በሁለቱም ከተሞች በሺሆች የሚቆጠር ሰው ዛሬ፤ ሐምሌ 7 / 2005 ዓ.ም አደባባይ መውጣቱን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ መሪዎች ማምሻውን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ከአንድነት ሰልፎች - ሐምሌ 7 / 2005 ዓ.ም
ከአንድነት ሰልፎች - ሐምሌ 7 / 2005 ዓ.ም

በደሴው ሰልፍ ላይ ሃምሣ ሺህ ይገመታል ያሉት ሰው መውጣቱን በፓርቲያቸው በኩል በቡድን መሪነት የተላኩት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ይህንን ሰልፍ ለማዘጋጀት ሰሞኑን ጥረት ያደርጉ በነበረበት ወቅት አስተባባሪዎችን እየያዙ ሳያሣድሩ መልቀቅን፣ ፖስተሮቻቸውን መገነጣጠልና ጭቃ መቀባትን የመሣሰሉ አድራጎቶች የተፈፀሙባቸው መሆኑን አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡
ደሴ
ደሴ
ጎንደር ላይም የተካሄደው ሰልፍ ሊጠናቀቅ አሥር ደቂቃ ሲቀረው በከባድ ምክንያት ዝናብ መቋረጡን ለቪኦኤ የገለፁት የአንድነት የብሔራዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን ቁጥሩ ሃያ አምስት ሺህ የሚገመት ሰው መውጣቱን አመልክተዋል፡፡

ከጎንደር ሰልፍ አስተባባሪዎች መካከል ስምንት አባሎቻቸው በእሥር ላይ እንደሚገኙና ከአካባቢው ባለሥልጣናትም እርሣቸውን ለማነጋገር ፍቀደኛ የሆነ ሰው ማጣታቸውን አቶ ዘካርያስ ጠቁመዋል፡፡

ሁለቱም ሰልፎች የተጠናቀቁት በሰላም እንደሆነና እስከ ፊታችን መስከረም ባለው ጊዜም በአዲስ አበባና በደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች፣ እንዲሁም በመቀሌና በሌሎችም አካባቢዎች ተመሣሣይ ሰልፎችን ለማድረግ የያዙትን ዕቅድ እንደሚገፉበት የፓርቲው ኃላፊዎች ገልፀዋል፡፡

የ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” መርኃግብር ሰልፈኞች በደሴ እና/ወይም ጎንደር ከተሞች ከያዟቸው መፈክሮች መካከል “የሕሊና እሥረኞች ይፈቱ” የሚሉ፣ ሥርዓቱ ለሙስና መጋለጡን የሚናገሩ፣ የኑሮ ውድነትን የሚያማርሩ፣ እንዲሁም “በአባይ መገደብ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የግብፅ ይሁንታ አያስፈልገንም፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታችን ያለገደብ ይከበር፣ በሃገራችን ፍትሕ ናፈቀን፣ ሃገር በዕውቀት እንጂ በጉልበት አይገዛም፣ ሙስሊም አሸባሪ አይደለም፣ የሙስሊሙ ጥያቄ የሙስሊም መንግሥት መመሥረት አይደለም፣ አንድነት ፓርቲያችን መተንፈሻችን” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ሲያሰሙ እንደነበር ታውቋል፡፡

ለተጨማሪና ዝርዝር መረጃ፣ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ መሪዎችና የሰልፎቹን አስተባባሪዎች ቃለምልልሶችን የያዘውን ከዚህ ጋር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:19:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG