በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከፍተኛው ፍርድ ቤት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራርን ገሠፀ


የፓርቲው መሪዎች የፍርድ ቤቱ አድራጎት ድራማ ነው፤ አግባብነት የለውም ይላሉ።

(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ረጂስትራር ፊርማ ሐምሌ 26/2004 የወጣ ደብዳቤ ለአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ የተፃፈ መጥሪያ ይመስላል።

ከሣሽ ማን እንደሆነ መጥሪያው የሚለው ባይኖርም ተከሳሽ አቃቤ ሕግ መሆኑን ያሣያል።

የመጥሪያው ይዘት የሚያስረዳው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ የወንጀል ችሎት በተከሣሾች እነ አንዱዓለም አራጌ ላይ ሰኔ 21 እና ሐምሌ 6/2004 ዓ.ም. ያሳለፋቸውን ውሣኔዎች ተከትሎ ያወጣቸውን መግለጫዎች በተመለከተ ፍርድ ቤቱ የፓርቲውን ሊቀመንበር ወይም ምክትል ሊቀመንበር ወይንም ተወካይ ማነጋገር መወሰኑና የተወከለው ሰው ሐምሌ 27/2004 ዓ.ም. ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ተኩል እንዲቀርብ የሚያዝዝ ነው።

ፍርድ ቤቱ ያሳለፈውን ውሣኔና የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ አመራር አባላት የሰጡትን መልስ ዝርዝር ከመለስካቸው አምኃ ዘገባ ያድምጡ።

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )


XS
SM
MD
LG