በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቶ ግርማ ሠይፉ እና የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ተይዘው ተለቀቁ


አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ
አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ

ከተያዙት መካከል አንዱ “እጃቸው ያለመያዝ መብት” ያላቸው እንደራሴ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ግርማ ሠይፉ እንደሆነም ታውቋል፡፡




ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ - የአንድነት ሊቀመንበር
ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ - የአንድነት ሊቀመንበር

please wait

No media source currently available

0:00 0:17:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ የአመራር አባላት ዛሬ ለሦስት ሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው መለቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡

ከተያዙት መካከል አንዱ “እጃቸው ያለመያዝ መብት” ያላቸው እንደራሴ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ግርማ ሠይፉ እንደሆነም ታውቋል፡፡

በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት ሌሎች የፓርቲው አመራር አባላት መካከል ሊቀመንበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ዋና ፀሐፊው አቶ አሥራት ጣሴ፣ የሥራ አመራር ኮሚቴው አባልና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ዳንኤል ተፈራና ምክትላቸው አቶ ሃብታሙ አያሌው፣ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባላት አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ስዩም መንገሻ እና አቶ ሺመልስ ሃብቴ፣ የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን፤ እንደሁም ሰላሣ ሦስቱ እየተባሉ ከሚጠሩት ስብስብ መካከል የሆኑ ሌሎችም ፓርቲዎች መሪዎች እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡
ግርማ ሠይፉ - እንደራሴ
ግርማ ሠይፉ - እንደራሴ

ለአራት ሰዓታት ያህል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የቆዩት የፓርቲው መሪዎች የተለቀቁት በማስጠንቀቂያ ሲሆን ሌሎች የፓርቲው የአዲስ አበባ አባላት የሆኑና ፖስተር ሲበትኑ የነበሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ወጣቶችን በዋስ ለማስለቀቅ እየተጣደፉ እንደነበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪና ዝርዝር መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG