በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአንድነት መሪዎች ከአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኙ


የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ አሥራት ጣሴ እና የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ
የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ አሥራት ጣሴ እና የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:37 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በጎንደርና በደሴ ከተሞች ሕዝባዊ ሰልፎችን ያካሄደው የአንድነት ከፍተኛ መሪዎች የአባሎቻቸውን ጎንደር ውስጥ መታሠር ጨምሮ ደርሰውብናል የሚሉትን አቤቱታ ለክልሉ ፕሬዚዳንት ለአቶ አያሌው ጎበዜ ባሕርዳር ላይ ተገኝተው ማሰማታቸውን ገልፀዋል፡፡

የክልሉ ፕሬዚዳንት ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተሉ የገለፁላቸው መሆኑን መሪዎቹ አመልክተዋል፡፡

የክልሉን ፕሬዚዳንት ባሕር ዳር ቢሯቸው ሄደው ያነጋገሩት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ አሥራት ጣሴ እና የፓርቲው የብሔራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን የአቶ አያሌው ጎበዜን አቀባበልና አነጋገር “በሌሎች አካባቢዎች እምብዛም ያላየነው ጨዋነት የተመላበትና ደረጃውን የጠበቀ ነበር” ብለውታል፡፡

ለዝርዝርና ተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG