በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት የኢትዮጵያ ጉብኝት

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የህዝብ፣ የጥገኛነት ጠያቂዎችና የስደት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ረዳት ሚኒስትር ኤሊዛቤጥ ካምፕቤል ስደተኞችና ተፈናቃዮች የሚገኙበትን ሁኔታ ይበልጥ ለመረዳት ጋምቤላ፣ ሰመራና አዲስ አበባን ጎብኝተዋል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለቪኦኤ በላከው መግለጫ ካምፕቤል በሰመራ ቆይታቸው ከከተማዪቱ ከንቲባ አብዱ ሙሣና ከአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ ሞሃመድ ሁሴንቶ ጋር መገናኘታቸውንና በክልሉም ሆነ በአጠቃላይ ሃገሪቱ ውስጥ ሰዉ ላይ የተጋረጡ ባሏቸው ችግሮች ላይ መወያየታቸውን አመልክቷል።

በተለይም የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮችን አያያዝ በተመለከተ ሃሳብ መለዋወጣቸውንና ከንቲባ አብዱ ሙሳ የአሜሪካ መንግሥት ለአፋርም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ እያደረገ ስላለው ድጋፍ ማመስገናቸውን የኤምባሲው መግለጫ ጠቁሟል።

ካምፕቤልና የልዑካን ቡድናቸው በሰርዶ ስደተኞች ጣቢያ ተገኝተውም ከነዋሪዎቹና ጣቢያውን ከሚያስተዳድሩት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረዋል።

በአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ የተቋቋሙትን በማንኛውም የአየር ጠባይ ውስጥ የሚያገለግሉ መጠለያዎችን፣ የውኃና የንፅህና መጠበቂያ አገልግሎቶችንና ሌሎችን ፕሮግራሞችን መጎብኘታቸውን ከአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መግለጫ አመልክቷል።

ዲፕሎማቷና ቡድናቸው በጋምቤላም ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጋቸውን ትናንት መዘገባችን ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG