በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱርክና የአውሮፓ እሰጥ አገባ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በቱርክና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱን በአህጉሪቱ ውስጥ ባለው የስደት ጉዳይ ላይ አሳሳቢ ጥላ እንዲያርፍ ማድረጉ ተገለፀ፡፡

በቱርክና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱን በአህጉሪቱ ውስጥ ባለው የስደት ጉዳይ ላይ አሳሳቢ ጥላ እንዲያርፍ ማድረጉ ተገለፀ፡፡

በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው መካረር እየተባባሰ የመጣው የቱርክን ፕሬዚዳንት የሥልጣን ዘመን ለማራዘም በሚያስችል ሁኔታ ሕገ መንግሥቱን ለመቀየር ይደረጋል ለተባለው ውሣኔ ሕዝብ የአንካራ ሚኒስትሮች በአውሮፓ ሃገሮች ውስጥ ቅስቀሳዎችን እንዳያካሂዱ ከታገዱ በኋላ ነው፡፡

የቱርክ የአውሮፓ ኅብረት ጉዳዮች ሚኒስትር ኦመር ሴሊክ ዛሬ ኢስታንቡል ላይ የሠነዘሩት ኃይለ-ቃል መፋጠፋና ንትርኩን ከፍ ወዳለ መካረር እንደገፋው ነው እየተነገረ ያለው፡፡

ቱርክ ግዴታዎቿን ብትወጣም የአውሮፓ ኅብረት ግን በተስማሙት መሠረት የሚጠበቅበትን አለመፈፀሙን ጠቁመዋል፤ እንዲያውም “ቃሉን አጥፏል” ሲሉ ከስሰዋል ሚኒስትሩ፡፡

ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የቱርክና የአውሮፓ እሰጥ አገባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:53 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG