በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ህጋዊ ሰነድ ስለሌላቸው የውጭ ሀገር ፍልሰተኞች


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ህጋዊ ሰነድ ስለሌላቸው የውጭ ሀገር ፍልሰተኞች ፍርሃት የሚያቀጣጥል መግለጫ መስጣታቸውን እንደገና ተያይዘውታል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ህጋዊ ሰነድ ስለሌላቸው የውጭ ሀገር ፍልሰተኞች ፍርሃት የሚያቀጣጥል መግለጫ መስጣታቸውን እንደገና ተያይዘውታል።

በደቡቡ ድንበር በኩል ለመግባት እየተጓዙ ያሉትን ጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የሚገድብ አስፈጻሚ ትዕዛዝ በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ እንደሚያስተላልፉ ዝተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ትናንት ሃሙስ ሚዙሪ ክፍለ ሃገርዋ ኮሎምቢያ ከተማ በአንድ የፖለቲካ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለተወለደ ማናቸውም ሰው የሀገሪቱን ዜግነት የሚያረጋግጠውን የህገ መንግስሥቱን አሥራ አራተኛ ማሻሻያ አስቀይራለሁ በማለት በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

ነፍሰ ጡር የውጪ ሃገር ሴቶች ልጆቻቸው አሜሪካዊ ዜግነት እንዲያገኙ የሚመጡበት “የወሊድ ቱሪስትነት” ያሉትን እንደሚቃወሙ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

የህገ መንግሥቱን አስራ አራተኛ ማሻሻያ በአስፈፃሚ ትዕዛዝ መቀየር እንደሚችሉ ገልፀዋል። ይሁን እንጂ የህግ ተንታኞች ግን ህገ መንግሥቱን በቀላሉ በማስፈፀሚያ ትዕዛዝ መቀየር እንደማይቻል አጥብቀው ይሟገታሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG