በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሜኔሶታ የሚገኙ የሶማሌ ማህበረሠብ አባላት በሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ንግግር ማዘናቸውን ገለፁ


ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ
ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ

“የሜኔሶታ ህዝብ በሶማሊያ ስደተኞች ምክንያት መከራውን አይቷል” ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ አነጋገራቸውም ማህበረሠቡን እንዳሳዘነ ተጠቅሷል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ሜኔሶታ አውሮፕላን ጣቢያ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ሲናገሩ ነው ይህን ያሉት።

ትራምፕ ዲሞክራትዋን ተፎካካሪያቸው ሂላሪ ክሊንተንን የውጭ ሀገር ዜጎች ያለምንም ገደብ እንዲገቡ እጅግ አደገኛ ከሆኑ የዓለም አካባቢዎች ስደተኞችን እንዲመጡ ነው የሚፈልጉት ብለው ይወነጅሏቸዋል።

“ይህን ጉዳይ ደግሞ እናንተ ከማንም በላይ ታውቁታላችሁ” ሲሉ ደጋፊዎቻቸው “ሆ” ብለው ተቀብለዋል።

“ሜኔሶታ ውስጥ ስደተኛ በደምብ ጉዳዩ ሳይጣራ እንደሚገባ እናንተ በደምብ ታውቁታላችሁ። ብዛት ያላቸው ሶማሌ ስደተኞች እናንተ ሳታውቁ፣ ሳትደግፉ፣ ሳትፈቅዱ ወደክፍለ ሀገራችሁ ይመጣሉ" ብለዋል - ሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ፡፡

በሜኔሶታ የሚገኘው የሶማሌ ማህበረሠብ አባላት ይህን የሚስተር ትራምፕን ውርጂብኝ አውግዙዋል።

ፕሮፌሰር አብዲ ኢስማኤል ሳማተር በሜኔሶታ ዩኒቨርስቲ የመልክዓ ምድርና የተፈጥሮ አካባቢ ክፍል ሊቀመንበር ናቸው።

“የትራምፕ ንግግር አሳዝኝና አስቀያሚ ነው፤ ይቺን ሃገር ሰዎች በዘራቸው፣ በቀለማቸው፣ በፆታቸው አድልዎ ሲደረግባቸው ወደነበረው ወደቀድሞው ዘመን የሚመልስ አሳዛኝ ..” ብለዋል - የሶማሌ ተወላጁ ምሁር

የቪኦኤ የሶማሊኛ አገልግሎት ዘጋቢ ሃሩን ማሩፍ ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጂት ታየ ታቀርበዋለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በሜኔሶታ የሚገኙ የሶማሌ ማህበረሠብ አባላት በሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ንግግር ማዘናቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:39 0:00

XS
SM
MD
LG