የፕሬዚዳንቶችን እና ሌሎች ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናትን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት የተጣለበት ብሄራዊ ተቋም ድሬክተር ኪምበርሊ ቼትል ይህን የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት በጠራው ሥነ ስርአት ተገኝተው ምላሽ በሰጡት ወቅት ነው።
አንድ የታጠቀ ወጣት የምርጫ ዘመቻ እየተካሄደ ካለበት ሥፍራ አቅራቢያ ከሚገኝ አንድ መጋዘን ጣሪያ ላይ ከወጣ በኋላ፣ ማንም ሳያስቆመው በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ማድረግ በመቻሉ ድርጅታቸው “በአስርት ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማያውቅ እና እጅግ ጉልህ” ያሉትን “የአሠራር ድክመት አሳይቷል” ብለዋል።
በአንዲት የፔንስልቬንያ ክፍለ ግዛት ውስጥ በምትገኝ ገጠራማ አካባቢ ሜዳ ላይ ይካሄድ በነበረው የምረጡኝ ዘመቻ እንቅስቃሴ ወቅት በትራምፕ ላይ የተፈጸመውን የግድያ ሙከራ አስመልክቶ የምስክሮችን ቃል ለመስማት በዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት የቁጥጥር እና የተጠያቂነት ኮሚቴ የተጠራው ሥነ ስርአት ከመካሄዱ አስቀድሞ ቼትል ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር “በሃምሌ ስድስቱ ክንውናችን ወድቀናል” ብለዋል።
በድርጅቱ ውስጥ 30 አመታት ለሚጠጋው ጊዜ ያገለገሉት ቼትል፤ በትራምፕ ላይ ለደረሰው ጥቃት ያበቋቸውን ድክመቶች ለማስተካከል ቃል ገብተዋል። ይሁን እንጂ በርካታ የምክር ቤት አባላት ግን ቼትል ‘ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ይልቀቁ’ አለያም ፕሬዝዳንት ባይደን ከሥራ ያሰናብቷቸው’ ሲሉ መጠየቃቸው ተዘግቧል።
መድረክ / ፎረም