የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሳውዲ ዓረብያ ውስጥ ባደረጉት በሰፊው ሲጠበቅ የቆየ ንግግራቸው ሙስሊም መሪዎች ፅንፈኝነትን ጨርሶ እንዲደመስሱ ተማፃኑ።
“ጦርነቱ በመልካምነትና በከበደ ዕኩይነት መካከል ነው” ሲሉ ገልፀውታል ፕሬዚዳንቱ።
የሀገራቸውን የመካከለኛ ምስራቅ ፖሊሲም ዘርዝረው አስረድተዋል።
ትናንት ዕሁድ ሚስተር ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትነት የመጀመሪያቸው በሆነው የውጭ ጉብኝት በቀዳሚነት በጎበኙዋት የሳውዲ ዓረብያ ዋና ከተማ ሪያድ ያደረጉት ንግግር ለሙስሊም መሪዎች የመልሶ ዕርቅ መልዕክትና ጠንካራ ፈተና ጥሪም የተላበሰ ነበር።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ