በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶናልድ ትረምፕ እና ኩባንያቸው ማጭበርበር ፈጽመዋል ሲሉ እንድ የኒው ዮርክ ዳኛ ወሰኑ


የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ
የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ

የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕና ግዙፍ የግንባታ ኩባንያቸው ለዓመታት ማጭበርበር ፈጽመዋል ሲሉ አንድ በኒው ዮርክ የሚገኙ ዳኛ ወስነዋል።

የቀድሞው ፕሬዝደንት እና በአሜሪካውያን ዘንድ እንዲታወቁ እና ለዋይት ሃውስም ያበቃቸው ግዙፍ የግንባታ ኩባን ያ፤ ባንኮችን፣ የመድሕን ኩባንያዎችን፣ እና ሌሎችንም፤ የያዙትን የሃብት መጠን እጅግ አጋኖ በማቅረብ፣ ብድር ለማግኘት እና ሌሎችንም ስምምነቶች ለመፈጸም ተጠቅመዋል ሲል ክሱ ገልጿል።

የዳኛው ውሳኔ ከከሳሽ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ለሊታ ጄምስን ዋና የክስ ጭብጥ ጋር የተስማማ ሲሆን፣ ሌሎች ስድስት ክሶች ገና ውሳኔ አላገኙም ተብሏል።

ከሳሽ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ለሊታ ጄምስ፣ የ 250 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት እና ዶናልድ ትረምፕ መኖሪያቸው በሆነው ኒው ዮርክ ግዛት ወደ ፊት ሥራ እንዳይሠሩ እንዲወሰንላቸው ጠይቀዋል።

ትረምፕ ምንም ጥፋት እንዳልፈጸሙ ሲገልጹ ቆይተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG