ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከአውሮፓ ኅብረት፣ ከካናዳና ከሜክሲኮ ለሚላኩት አሉሙኒየምና ብረታብረት ላይ ከሚደነግጉት ቀረጥ ቢያንስ በአንድ ተጨማሪ ወር ነፃ የማድረግ ዕቅድ እንዳላቸው ታውቋል።
የተጠቀሱት ሀገሮች በቻይና፣ በጃፓንና በሩስያ ላይ ከተደነገገው ቀረጥ በጊዚያዊ መልክ ነፃ እንዲሆኑ የተደረገው ውሳኔ ዛሬ ሊያበቃ ነበር።
የዋይት ኃዋስ ቤተመንግሥት በመካሄድ ላይ ያለውን ድርድር ሥምምነት ላይ ለማድረስ እንዲቻል የሠላሳ ቀናት ጊዜ እንደሚስጥ ተናግሯል።
የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መገለጫ በጊዚያዊ መልክ የማራዘሙን ተግባር ነቅፏል። የአውሮፓ ኅብረት ስለጉዳዩ የመደራደር ፍላጎት አለው ሆኖም “በዛቻ አይደራደርም” ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ