በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ብሪታንያን እየጎበኙ ነው

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ብሪታንያን እየጎበኙ ነው። ከንጉሣዊው ቤተሰብ ጋር ተገናኝተው መነጋገርን ያካትታል። የእራት ግብዣ ይደርግላቸዋል። ከሥልጣን ለመሰናበት ማመልከቻ ካስገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ። ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ባኪንግሀም ቤተ-መንግሥት ሲደርሱ የብሪታንያዋ ንግሥት ኤልዝበት ፕሬዚዳንቱንና ባለቤታቸው ሜላንያ ትረምፕን ተቀብለዋል።

የ41 መድፎች ተኩስንና የቤተመንግሥት የክብር ዘብ ፍተሻን ያከተት የአቀባበል ሥነ-ስርዓት ከተደረገላቸው በኋላ ከንግሥቲቱ ጋር ምሳ በልተዋል። ንግሥት ኤልዝበት ፕሬዚዳንቱንና ባለቤታቸውን የባኪንግሀም ቤተመንግሥት የስዕል ቤተመዘክራን አስጎብኝተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG