በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ የማይክ ፓምፔዮን ሹመት ለማስተጓጎል ዴሞክራቶቹ እየጣሩ ነው አሉ

ማይክ ፓምፔዮ
ማይክ ፓምፔዮ

ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያጯቸውን የስለላ ተቋሙን ዳይሬክተር ማይክ ፓምፔዮን ሹመት ለማስተጓጎል ዴሞክራቶቹ እየጣሩ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ክስ አሰሙ።

ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያጯቸውን የስለላ ተቋሙን ዳይሬክተር ማይክ ፓምፔዮን ሹመት ለማስተጓጎል ዴሞክራቶቹ እየጣሩ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ክስ አሰሙ።

የሚስተር ፓምፔዮ ጉዳይ ሪፐብሊካኑ ሴናተሮች አሥራ አንድ ለአሥር አብላጫ ባላቸው በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቴ ውስጥ ብርቱ ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑ ታውቋል።

የኮሚቴው አባላት ዛሬ ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ሲሆን አሥሩም ዴሞክራቶችና ከሪፐብሊካኑ ደግሞ ራንድ ፖል የፓምፔዮን መጭው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሆን እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል።

ይሁን እንጂ የዕጩው ሹመት ወደ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ሙሉ መድረክ ለድምፅ እንደሚላክ ተገልጿል።

ዴሞክራቶቹን “ነገር አስተጓጓዮች” ሲሉ ጠርተዋቸዋል ፕሬዚዳንት ትረምፕ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ዕጩአቸው ላይ ስለያዙት አቋም ቅሬታቸውን ሲገልፁ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG