በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ትረምፕ አማካሪ ስቲቭ ባነን እጃቸውን ሰጡ


የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የረጀም ጊዜ አጋርና አማካሪ የነበሩት ስቲቭ ባነን
የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የረጀም ጊዜ አጋርና አማካሪ የነበሩት ስቲቭ ባነን

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የረጀም ጊዜ አጋርና አማካሪ የነበሩት ስቲቭ ባነን ዛሬ ሰኞ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ ቀርበው መታሰራቸውን ሮይተርስ ዘገበ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤትን በመድፈር ሁለት ወንጀሎች የተፈላጊ የነበሩት ባነን፣ እጃቸውን ለመስጠት ወደ መጡበት የኤፍቢአይ ህንጻ ከመግባታችው በፊት በካሜራ ፊት "የባይደንን አስተዳደር እናስወግዳለን" ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የዩናይትድስ ስቴትስ የፍትህ ሚኒስቴር ባላፈው ሳምንት፣ እኤአ ጥር 6 በምክር ቤቱ ህንጻ የተካሄደውን አመጽ የሚመረምረውን ምክር ቤት ኮሚቴ ጥሪ ባላመቀበል በ67 ዓመቱ ስቲቭባነን ላይክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡

ባነን ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ቢያንስ ከ30 ቀናት እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ እስር ሊቀጡ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG