በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ እና መገናኛ ብዙሃን


ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሚድያና ፕሬዚዳንቶች ብዙም ፍቅር ባይንፀባረቅባቸውም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሥልጣን ከተረከቡ ወዲህ ሚድያን እንደ ጠላት የማየቱ ሁኔታ እየተባባሰ ሄዷል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሚድያና ፕሬዚዳንቶች ብዙም ፍቅር ባይንፀባረቅባቸውም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሥልጣን ከተረከቡ ወዲህ ሚድያን እንደ ጠላት የማየቱ ሁኔታ እየተባባሰ ሄዷል።

ትራምፕ ሚድያን “የህዝብ ጠላት” የሚል ስም ለጥፈውበት በተደጋጋሚ ይጠቀሙበታል። መገናኝ ብዙሃንን “አደገኛና በሽተኛ” ከማለት አልፈው “ጦርነት ሊያስነሳ ይችላል” በሚል ተንብየዋል።

አንዳንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን አካላት ታድያ ፕሬዚዳንት ትረምፕ በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚሰነዝሩት ልፈፋ ከልኩ አልፏል፣ አደገኛ ነው እያሉ ናቸው።

በሀገሪቱ ዙሪያ ያሉት ጋዜጠኞች በቦስተን ግሎብ አስተባባሪነት ዛሬ ባልተጠበቀ ሁኔታ የተቀናጀ የርዕሰ አንቀጽ ዘመቻ ጀምረዋል።

ዘመቻው የተከፈተው “በነፃ ፕሬስ ላይ ያነጣጠረው ቆሻሻ ጦርነት ማቆም አለበት” በሚል ርዕስ ነው።

ከሁለት ምዕተ ዓመታተ በላይ ለሆነ ጊዜ የአሜሪካ መሰረት የሆነው መርህ የሀገሪቱን ጋዜጣኞች መብት ሲያስከብር ኖሯል። ለውጭ ሃገራትም ተምስሌት ሆኖ ቆይቷል። አሁን ግን ከባድ አደጋ ላይ ወድቋል። ከአንካራ እስከ ሞስኮ ቤዢንግና ባግዳድ ድረስ ላሉት አምባገነን መንግሥታት ጋዜጠኞች እንደሀገር ጠላት ሊታዩ እንደሚችሉ የሚያሳይ መጥፎ አርአያ ነው” ይላል “ዘ ግሎብ”ያወጣው ርዕሰ አንቀፅ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG