በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያ በአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ ከ30 በላይ ሰዎች ሞቱ


በናይጄሪያ ሰሜን ምስራቃዊ ቦርኖ ክፍለ ግዛት በደረሱ ሦስት አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃቶች ቢያንስ ሰላሳ ሰዎች ሲገደሉ፣ ሊሎች አርባ ሰዎች እንደቆሰሉ ተገለፀ።

የሀገሪቱ ባለሥልጣናት እንዳሉት አንደኛው ጥቃት የደረሰው ኮንዱጋ በተባለ መንደር እሁድ ማታ ነዋሪዎች ተሰብስበው ቢራ እየጠጡ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያ በቴሌቭዥን በመመልከት ላይ እያሉ ነበር።

ብዙ ሰው ሊሞት የቻለው ለመንደሩ ቅርብ የሆኑ በቂ የአጣዳፊ ዕርዳታ ጣቢያዎች ባለመኖራቸው ነው ሲሉም ባለሥልጣናቱ አክለዋል። ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ የለም። ተጠርጣሪው ቡድን ቦኮ ሃራም መሆኑ ተዘግቧል።

የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሞሃማዱ ቡሃሪ “አረመኒያዊ” ሲሉ የጠሩትን ጥቃት አውግዘው ለደኅንነት በሚያሰጉ ሥፍራዎች ጥበቃው እንዲጠናከር አሳስበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG