በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዲስ አበባው መንፈሳዊ ኰሌጅ እንደተዘጋ ነው፤ ጉዳዩ ሕግ ፊት ቀርቧል


በቅድስት ሥላሴ መንፈሣዊ ኮሌጅ ቅጥር ውስጥ የሚገኝ ታሪካዊ ሕንፃ
በቅድስት ሥላሴ መንፈሣዊ ኮሌጅ ቅጥር ውስጥ የሚገኝ ታሪካዊ ሕንፃ


መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል

please wait

No media source currently available

0:00 0:19:52 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳ ኰሌጅ ተደጋግሞ ሲዘጋና ሲከፈት ቆይቷል።

ከወር በፊት ተማሪዎቹ «ያቀረብነው ጥያቄ እስኪመለስ» በሚል ቢያቋርጡም ፓትርያርኩ «እየተማራችሁ ጥያቄው ይታያል» የሚል መልስና መመሪያም ስለሰጡ ትምህርቱ ተጀመረ።

አሁን የሁሉንም መምህራን ክፍል እየተከታተሉ ነገር ግን እንዲነሱላቸው የጠየቋቸው መምህራን ወደ ክፍል ሲገቡ እየጣሉ በመውጣታቸው፣ አስተዳደሩ «የእነሱን ትምህርት ካልተማራችሁማ እዘጋዋለሁ» ብሎ መጋቢት 30 ቀን «ኰሌጁ ከዛሬ ጀምሮ ተዘግቷል» የሚል ማስታወቂያ ለጠፈ።

አሁን ድረስ ኰሌጁ እንደተዘጋ ሲሆን፣ ተማሪዎቹም ያለ ምግብ እየተራቡ መቀጠል ስላቃታቸው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል።

ፍርድ ቤቱም «የተወሰኑ ተማሪዎች ወክሉ እንጂ ሁላችሁም መምጣት የለባችሁም ስላለ፣ ተወካዮች ተመርጠው ጉዳዩ በፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡

ለመሆኑ መጨረሻው ምንድነው?

ቀሲስ ዶ/ር ምክረሥላሴ ገብረአማኑኤል፣ በኰሌጁ ከተማሪነት እስከ መምህርነት፣ ቀጥሎም በጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅነት ያገለገሉ ሲሆኑ አሁን በአፍሪቃ የዓለምአቀፍ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ዋና ፀሐፊ ናቸው። ከኰሌጁ ቀደም ብለው የተመረቁና አሁንም በተመላላሽ መምህርነት የሚያስተምሩት መምህር ተመስገን ዮሐንስ፣ እንዲሁም፣ የኰሌጁ የተማሪዎች መማክርት ፕሬዚደንት ዲያቆን ታምርአየሁ አጥናፌ በጉዳዩ ዙሪያ ከቪኦኤ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አዲሱ አበበ ነው ያወያያቸው፤ ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG