እየሩሳሌም የህፃናትና ማኅበረሰብ ልማት የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ነበሩ ላላቸው 91 ወጣት ሴቶች ስልጠና እና የመስሪያ ገንዘብ በመስጠት በተለያየ ሞያ ማሰማራቱን አስታወቀ።
ድርጅቱ በቅርቡ ባዘጋጀው የማበረታቻ ሽልማት እያንዳንዳቸው 20ሺህ ብር ተቀብለው በመረጡት የሞያ መስክ የተሰማሩት ወጣት ሴቶች ከአንድ ዓመት በኋላ በጥሩ የህይወት መስመር ላይ መሆናቸውን በሰጡት የምስክርነት አስተያይት አመለከቱ።