በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተገደሉና የተማረኩ የሕወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ባለሥልጣናት ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ


የሀገር መከላከያ ሰራዊት በቅርቡ በተወሰደ እርምጃ የተገደሉና የተማረኩ የሕወሓት ወታደራዊ መኮንኖች እና ባለሥልጣናት ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያው መከላከያን ጠቅሶ ባስተላለፈው ዜና፤ የማይካድራውን ጭፍጨፋ መርተዋል ብሎ መንግስት የሚጠረጥራቸው ኮሎኔል የማነ ገብረሚካኤልን ጨምሮ ቁጥራቸው በርከት ያሉ የወታደራዊ ባለሥልጠናት ተገድለዋል።

የትራንስፖርት የቀድሞ ሚኒስትር ዴኤታ ሙሉ ገብረእግዚአብሄር ደግሞ እጅ ከሰጡት ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል። እጃቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መገደላቸው ከነገረላቸው መካከል ኮሎኔል ዓለም ገብረመድህን፣ ኮሎኔል ቢንያም ገብረመድህን፣ ኮሎኔል አምባዬ፣ ኮሎኔል ማሾ፣ ኮሎኔል ይርጋ ስዩም፣ ኮሎኔል ሃዱሽ፣ ኮሎኔል አጽብሃ፣ ኮሎኔል ተስፋዬ ገብረመድህን፣ ኮሎኔል ዮሃንስ ካልአዩ፣ ኮሎኔል ተክለእግዚአብሄር፣ ሌተናል ኮሎኔል ብርሃኔ ቶላ እና ሌሎች በስም ያልተገለጹ 4 ኮሎኔሎችና ሁለት የዞን አመራሮች ይገኙበታል ተብሏል።

XS
SM
MD
LG