በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመቀሌ የሕወሃት ዝግ ስብሰባ እየተካሄደ ነው


መቀሌ
መቀሌ

በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለውን የሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ሕወሃት/ ዝግ ስብሰባ ሁለት አባላት ረግጠው እንደወጡ ታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለውን የሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ሕወሃት/ ዝግ ስብሰባ ሁለት አባላት ረግጠው እንደወጡ ታውቋል፡፡

ከባድ ሂስና ግለሂስ በተደረገበት ወቅት ስብሰባውን ረግጠው የወጡት የማዕከላዊ አባላት ወ/ሮ አዜብ መስፍንና አቶ ብርሃነ ኪዳነማሪያም መሆናቸው ታውቋል፡፡

ማንነታችው እንዳይገለፅ የጠየቁ ምንጮች በተናገሩት መሠረት ከአንድ ሳምንት በላት በተካሄደው ስብሰባ አባላቱ በሦስት ተከፋፍለው የሞቀ ክርክር ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡

አንደኛው ወገን አሁን በአለው የፓርቲው የፖለቲካ አመራር የረካ፣ ሌላው በፖለቲካው ፓርቲ ሥራ ጥሩም መጥፎም ይስተዋላል የሚል፣ ሦስተኛው ደግሞ የፖለቲካ ሂደቱ ጥሩ ባለመሆኑ ሥር ነቀል ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል የሚሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ስብሰባው እየተገባደደ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ “ተፈጠረ” የተባለውን አለመግባባትና ስብሰባ ረግጠው ወጡ የተባሉት እነማን እንደሆኑ ዛሬ ለማጣራት ሞክረናል።

ትዝታ በላቸው በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት ከህወሃት መሥራች አባልና የአሁኑ የዓረና ትግራይ አመራር አባል ከአቶ ገብሩ አሥራትና ከሌሎች እንግዶች ጋር ለዛሬ የነበራትን ቀጠሮ አጋጣሚ በመጠቀም ስለ መቀሌው የሕወሃት ስብሰባም አንስታላቸዋለች።

ውይይቱ የተካሄደው ቀደም ያለው ዜና ከመገለፁ በፊት መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

ከአቶ ገብሩ አሥራት ጋር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲሥነ ጥበባት ኮሌጅየኢትዮጵያ የሥነ ጥበብ መምህር አቶ አበባው አያሌው ይገኛሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በመቀሌ የሕወሃት ዝግ ስብሰባ እየተካሄደ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:29 0:00
በመቀሌ የሕወሃት ዝግ ስብሰባ እየተካሄደ ነው - ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:43 0:00
በመቀሌ የሕወሃት ዝግ ስብሰባ እየተካሄደ ነው - ክፍል ሦስት
please wait

No media source currently available

0:00 0:21:25 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG