በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአቶ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት አመራሮች ጉባኤ ለማካሄድ እየተዘጋጁ መሆኑን ገለፁ


በአቶ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት አመራሮች ጉባኤ ለማካሄድ እየተዘጋጁ መሆኑን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:00 0:00

በነሐሴ ወር 2016 በተካሄደውና ምርጫ ቦርድ እውቅና ባልሰጠው የህወሓት ጉባኤ ያልተሳተፉት፣ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት የህወሓት አመራሮች ህጋዊ ሲሉ የገለፁትን 14ኛ ጉባኤ ለማካሄድ እንደተዘጋጁ ገልፀዋል ።

የአቶ ጌታቸው ቡድን አባላት ለሁለት ቀናት ባካሄዱትና "ህወሓትን የማዳን" በማለት በጠሩት ስብስባ ላይ ከተሳተፉት አመራሮች አንዱ አቶ በየነ መክሩ “ህወሓት ጉባኤውን ስላላካሄደ ለማካሄድ እየተዘጋጀን ነን” ብለዋል።

በዚህ ጉዳይ የሌላኛውን የህወሓት ቡድን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራውና ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ያካሄደው ሌላው ቡድን፣ በነሐሴው ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አድርጎላቸው ያልተገኙት እነዚህን 16 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ በፓርቲው ስም እንዳይንቀሳቀሱ ማገዱን በኋላም ከአባልነት ማገዱን ማስታወቁ ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG