በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዝግ ስብሰባ በመቀሌ

የሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዝግ ስብሰባ መቀሌ ከተማ ላይ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ከሥልጣን የተሰናበቱ አንጋፍ የድርጅቱ አባላትም ተገኝተውበታል።

የሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዝግ ስብሰባ መቀሌ ከተማ ላይ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ከሥልጣን የተሰናበቱ አንጋፍ የድርጅቱ አባላትም ተገኝተውበታል።

ሕወሃት የትግራይንና የኢትዮጵያን ሕዝብ በሚገባ አልመራም። አሁን የምንገኝበት አደጋ ላይ የወደቅነውም በሌሎቹ የትግል አጋሮቻችን በሆኑት ድርጅቶች ድክመት ሳይሆን ሥራችንንና ኃላፊነታችንን በተጠበቀብን መንገድ ባለመፈፀማች ነው። ሌላውን ሰበብ ማድረግ አይገባንም በሚል መንፈስ ማዕከላዊው ኮሚቴ ስብሰባውን ቀጥሏል ሲሉ ማንነታውን ለመግለፅ ያልፈለጉ ምንጮች ጠቁመዋል።

ግልፅነት በተመላበት መንፈስ የሚካሄደው ሂስና ግለ ሂስ በቃል ብቻ እንጂ የተሰውት ጓዶቻችንን አደራ በተግባር ላይ አላዋልንም በሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል ይላሉ ምንጮቹ።

በፊት የድርጅቱ የፖሊት ቢሮ አባላት በነበሩትና አሁን ባሉት አባላት ላይ ያተኮረ ሂስና ግለ-ሂስ እየተካሄደ መሆኑንም ምንጮቹ ገልፀዋል።

ሰብሰባው ገና እንደሚቀጥል ማንነታቸውን ለመግለፅ ያልፈለጉት ምንጮች አውስተዋል።

የሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዝግ ስብሰባ በመቀሌ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:10 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG