በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋና ማእከላዊ ባንክ ገዢ በፈቃዳቸዉ ስልጣን ለቀቁ


ፋይል ፎቶ - የጋና ማእከላዊ ባንክ በዋና ከተማዋ አክራ ውስጥ የፕሬዝደንት መንገድ በተሰኘው ቦታ ይገኛል እ.አ.አ. 20015
ፋይል ፎቶ - የጋና ማእከላዊ ባንክ በዋና ከተማዋ አክራ ውስጥ የፕሬዝደንት መንገድ በተሰኘው ቦታ ይገኛል እ.አ.አ. 20015

በአገሪቱ ኢኮኖሚ መላሸቅ በሚሰነዘርባቸዉ ሂስ የጋና ማእከላዊ ባንክ ገዢ በገዛ ፈቃዳቸዉ ስልጣን ለቀቁ።

ሄንሪ ኮፊ ዋምፓ (Henry Kofi Wampha) የአገሪቱን ዓመታዊ የባጀት መጓደል፣ እያሻቀበ የሄደዉን የዋጋ መናር፣ የጋናን ሚኒዛሬ ዋጋ እየቀነሰ መሄድ እና አገሪቱ ላይ እየተከመረ ለሄደዉ የዉጪ እዳ መፍትሔ እንዲሹ ነበር እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር በ 2012 የተሾሙት።

ዋምፓ አራት ዓመት ሊያገልግሉ ነበር የተሾሙት፤ ሆኖም ግን አንዳንዶች ስራቸዉ አስቸጋሪ መሆኑን ቢያምኑም ሂስ ስለሚሰነዘርባቸዉ ነዉ ሹመታቸዉን ለማጠናቀቅ ገና አራት ወር ሲቀራቸዉ ስልጣን የለቀቁት።

ፋይል ፎቶ - የካካዎ ገበሬዎች በምስራቃዊ ጋና በምትገኝ ከተማ አኪም እኮኮ (Akim Akooko) እ.አ.አ. 2012
ፋይል ፎቶ - የካካዎ ገበሬዎች በምስራቃዊ ጋና በምትገኝ ከተማ አኪም እኮኮ (Akim Akooko) እ.አ.አ. 2012

የጋና ኢኮኖሚ ጠበብት ፊሊክስ አሳንተ (Felix Asante) አዲሱ የማእከላዊ ባንክ ገዢ በድፍረት የመንግስትን ወጪ የሚቆጣጠር ሰዉ መሆን አለበት ይላሉ። "በእርግጥ በእግራቸዉ የሚሾመዉ ሰዉ፣ መንግስት ይህ ይከፈል ያ ሲላቸዉ ይህን ወጪ ማዉጣት አልቻለም ገንዘብ የለም ማለት መቻል አለበት።" ብለዋል።

ፋይል - ጋና ዋና ከተማ ውስጥ በአክራ የሚገኝ ማኮላ ገበያ እ.አ.አ. 2015
ፋይል - ጋና ዋና ከተማ ውስጥ በአክራ የሚገኝ ማኮላ ገበያ እ.አ.አ. 2015

በ2012 ስልጣን ሲይዙ ጋና ከፍተኛ የባጀት መጓደል ዉስጥ ነበረች። በዚያን ዓመት አገሪቱ አዲስ የምርጫ ቆጠራ ስርዓት ከመዘርጋት በተጨማሪ ለምርጫዉ ከፍተኛ ወጪ አድርጋለች። በጋና የፊታችን ሕዳር ወርም ሌላ ምርጫ ስለሚካሄድ ከፍተኛ ወጪ ይጠበቃል። በአገሪቱ አሳሳቢ የኢኮኖሚ ጉዳዮች የገንዘብ ዋጋ መቀነስና የዋጋ መናር ናቸዉ። አንድ አገር የምኒዛሪዋን ዋጋ መተመን የምትችለዉ የምታመርተዉንና የግል ነጋዴዎች ወደ ዉጭ መላክ ሲችሉ ነዉ ይላሉ የኢኮኖሚ ጠበብት። የጋና ፕሬዚደንት ቋሚ የማእከላዊ ባንክ ገዢ እስከሚሾሙ የሄንሪ ኮፊ ዋምፓ ምክትል የነበሩት ሚሊሶን ናራ (Millison Narha) በጊዜአዊነት ያገለግላሉ።

ፍራንቸስካ ካክራ ፎርሰን(Francisca Kakra Forson)ከአክራ የተጠናቀረውን ዘገባ ትዝታ በላቸው አቅርባዋልች፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የጋና ማእከላዊ ባንክ ገዢ በፈቃዳቸዉ ስልጣን ለቀቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG