በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወታደራዊ ባለሥልጣናቱ ዛሬም በአፍጋኒስታን ጉዳይ በምክር ቤቱ ፊት ይቀርባሉ


የመከላከያ ሚኒስትሩ ሊሎይድ ኦስትን፣ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጀኔራል ማርክ ሜሊ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ እዝ ዋና አዛዥ ጀኔራል ኬንዝ ፍራንክ መከንዚ፣
የመከላከያ ሚኒስትሩ ሊሎይድ ኦስትን፣ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጀኔራል ማርክ ሜሊ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ እዝ ዋና አዛዥ ጀኔራል ኬንዝ ፍራንክ መከንዚ፣

በአፍጋኒስታን ለሁለት አስርት ዓመታት የቆየውን ወታደራዊ ዘመቻ ፍጻሜና ከዚያች አገር ለወደፊቱ ሊነሳ ይችላል ስለተባለው ሽብርተኝነት ስጋት ለመገምገም ለተሰየሙት የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለማስረዳት የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ለሁለተኛ ቀን ዛሬም በምክር ቤቱ ይገኛሉ፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩ ሊሎይድ ኦስትን፣ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጀኔራል ማርክ ሜሊ፣ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ እዝ ዋና አዛዥ ጀኔራል ኬንዝ ፍራንክ መከንዚ፣ ከምክር ቤቱ የጦር መሳሪያ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ይቀርባሉ፡፡

ወታደራዊ ባለሥልጣናቱ በትናንትናው እለት የቀረቡት፣ በህግ መወሰኛው ምክር ቤት የጦር መሳሪያዎች ኮሚቴ ፊት ሲሆን፣ ሁለቱም ህግ አውጭዎች፣ በአገሪቱ ታሪክ ለረጅም ጊዜ የቆየው ጦርነት እንዲቆም የመደረጉን ውሳኔ የደገፉ ቢሆንም፣ በመጨረሻዎቹ ቀናት የነበረውን የአወጣጥ ሂደት አውግዘዋል፡፡

የመካለካያ ሚኒስትሩ ኦስትን የአወጣጡን ሂደት የተከላከሉ ሲሆን “በአሜሪካ በአየር የማጓጓዝ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ሲሆን፣ ይህም የተከናወነው በ17 ቀን ውስጥ ነው” ብለዋል፡፡

ጀኔራሉ አክለውም “በመጀመሪያ ለማውጣት ያቀድነው ከ70 እስከ 80ሺ ቢሆንም እኛ ግን ያወጣነው 124ሺህ ሰዎችን ነው” ብለዋል፡፡

"በሎጂስቲክ ደረጃ የተሳካ ቢሆንም እንደ ስትራቴጂ ግን የከሸፈ ነው” ያሉት ደግሞ የአገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮንን ጀኔራል ሜሊ ነበሩ፡፡

"የታሊባን ወደ ሥልጣን መምጣት በ20 ቀን ውስጥ የተከናወነ ሳይሆን በ20 ዓመታት ውስጥ ሲከማች የኖረ ነው" ብለዋል፡፡

እኤአ 2020 ዶሃ ላይ ከታሊባን ኃይሎች ጋር የተደረገው ስምምነት በአፍጋኒስታን ተዋጊዎች ላይ የሥነልቦና ተጽእኖ ማምጣቱንም ሜሊ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG