No media source currently available
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ህወሓት ሊጠቀምባቸው አስቧል ያላቸውን ኢላማዎች ከጥቅም ውጭ እያደረጋቸው መሆኑን ገለጸ። የመገናኛ ሥርዓቱን በማቋረጥ የሰሜን እዝን አስመትተዋል ያላቸውን ጀነራልና መኮንኖች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።