በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክስ


የኮቪድ-19 ዓለማቀፍ ወረርሽኝ እንደቀጠለ ቢሆንም የዘንድሮ የቶኪዮ ኦሊምፒክስ ዝግጅት መካሄዱ የማይቀር ነው ሲሉ የቶኪዮ 2020 ፕሬዚዳንት ዮሼሮ ሞሪ አስታወቁ።

ሞሪ ዛሬ ሰኞ በሰጡት መግለጫ መወያየት የሚያስፈልገው የቶኪዮ ኦሊምፒክስ ይካሄዳል በሚለው ሳይሆን እንዴት ይከናወን በሚለው ዙሪያ መሆን ይገባዋል ብለዋል።

የወረርሽኙ ይዞታ የፈለገውም ቢሆን ዝግጅቱ ውድድሮቹ መካሄዳቸው የማይቀር ነው ሲሉም የቶኪዮ ኦሊምፒክስ ፕሬዚዳንቱ አክለው አስገንዝበዋል።

እኤአ 2020 ሃምሌ ወር ታቅዶ የነበረው የቶኪዮ የበጋ ኦሊምፒክስ ውድድር በአንድ ዓመት እንዲራዘም ተደርጎ ዘንድሮሃምሌ 23/2021 እንደሚጀመር መታቀዱ ይታወሳል።

በበርካታ የዓለም ሃገሮች የእንቅስቃሴ ዕገዳ መታወጁ የኦሊምፒክስ ውድድሩ ይሳካል ወይ የምለውን ጥርጣሬ አባብሶታል።

ይህ በዚህ እንዳለ ብሪታንያ ውስጥ በመጀመሪያ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተከሰተው ዓይነት የኮሮናቫይረስ ዝርያ መዛመት በፈጠረው ስጋት የተነሳ የቤት ለቤት ምርመራ ዘመቻ ሊጀመር መሆኑ ተገለጠ።

በስምንት የብሪታንያ አካባቢዎች ነዋሪዎች በሙሉ በቫይረሱ የመያዝ ምልክት ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም ይመረመራሉ፤ በዘመቻው በአጠቃላይ ሰማኒያ ሽህ ሰዎች ይመረመራሉ ተብሏል።

XS
SM
MD
LG