No media source currently available
ወደ 2ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች እንደሚሣተፉበት የሚጠበቀዉና በጎንደር ከተማ የሚከበረው የጥምቀት በዓል በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ የፀጥታ ሥራዎችን መሰራታቸውን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለፁ፡፡ የጥምቀት በዓል በማይዳስሱ ቅርሶች ውስጥ የዓለም ቅርስ ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሣይንስ እና የባህል ድርጅት ዘንድሮ መመዝገቡ ይታወሳል፡፡