“ኢራን ለአካባቢዋ ስጋት ነች፣ እናም ቴህራን ላይ ከአሁኑ እርምጃ ካልተወሰደ ሥጋቱና አለመረጋጋቱ በመላው ዓለም ይሰስፋል” ሲሉ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቴለርሰን አሳሰቡ።
“ኢራን በመንግሥት ደረጃ ሽብርተኛነትን የምትደግፍ ሀገር ነች። በርካታ ውዝግቦችን የምታባብስና፣ ዩናይትድ ስቴትስም በየመን፣ በሦርያ፣ በኢራቅና በሊባኖስ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ የምታጣጥል፣ በእሥራኤል ላይም የሚካሄድ ጥቃትን የምትደግፍ ነች።”የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቴለርሰን።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ