ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉድይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንና የሩስያው አቻቸው ሰርጌ ላቨሮቭ በቅርቡ በኢትዮጵያ ጀምረው በየቅል ያተኩሩባቸውን የአፍሪካ ሀገሮች ጎብኝተዋል።
ቲለርሰን በአፍሪካ ጉብኝታቸው መሀል ከሥራ መባረራቸው ታውቋል። የሩስያ ፌደሬሽን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቨሮቭ ግን የኢትዮጵያን ዕዳ ከመሰረዝ አንስቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየእለቱ ወደ ሩስያ እስከመብረር ድረስ የሚሄዱ ስምምነቶች አድርገዋል።
በአፍሪካ ጉዳይ ጥናትና ምርምር የሚያደርጉት፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር አየለ በከሪስለጉብኝቶቹ ዓላማ፣ የቲለርሰን በአፍሪካ ጉብኝት ላይ እንዳሉ ከሥራ መባረር ምን ዓይነት መልዕክት እንደሚያስተላልፍ፣ ስለ ላቨሮቭ ጉብኝት ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
ሙሉውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ