በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰላም ጥበቃ ሥራ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ደቡብ ሱዳን ቀሩ


ፎቶ ፋይል፦ የጁባ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ
ፎቶ ፋይል፦ የጁባ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልእኮ መሰረት ደቡብ ሱዳን ተሰማርተው የነበሩ የትግራይ ተወላጅ ወታደሮች ከዚህ ቀደም ወደሀገራቸው የተመለሱ ተጋሩ የሰራዊቱ አባላት እስር ላይ ስለሚገኙ ለደኅነታትችን በመስጋት ወደ ኢትዮጵያ አንመልስም ሲሉ ለቪኦኤ ገለፁ።

እነዚህ የሰራዊቱ አባላት ባልደረቦቻቸው በሆኑት ሌሎች ወታደሮች ተደብድነናል፣ ወከባም ፈጽመውብናል ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል። ደቡብ ሱድን ውስጥ የፖለቲ ጥገኝነት በመጠየቅ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች አገልግሎት/ዩኤንኤችሲአር/ ከለላ ሥር እንደሚገኙም ድርጅቱ አረጋግጧል።

የትግርኛ አገልግሎት የስራ ባልደረባችን ገብረ ገብረመድህን ወታደሮችን፣ የጁባ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ኤቪየሽን የፀጥታና ደኅንነት ሃላፊ እንዲሁን /የዩኤንኤችሲአር/ መልስ በማካተት ያሰናዳው ዘገባ ይቀርባል።

አውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ከገቡ በኋላ ወደ ሃገራቸው አንመለስን ካሉት ወታደሮች አንዱ የሃምሳ አልቃ ለአከ ወልዳይ አውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ በሃይል ወደ ኢትዮጵያ ለመውሰድ ሲሉ የኢትዮጵያ ወታደሮቹ ደብድበውናል ብለዋል።

"ብዙ ችግር ነው ያሳለፍነው። ጁንታ ናችሁ ይሉና። ተጋሩ በመሆናችን ብቻ ትጥቃችንን አስፈትተው ሁላችንም ስንጠበቅ ነው የቆየነው። ጨንቆን ስለነበረ ይህ አጋጣሚ ተጠቅመን ጥገኛነት ለመጠየቅ አስበን ነበር። እኛን እሚደበድቡ ሰዎች መድበው በክላሽ አጅበው እስከ ኤርፖርቱ አስገብትውናል። ክላሽ ይዘው ወደ ውስጥ መግባት እንደማይችሉ ሲነግሯቸው ውስጥ ገብተን ቪዛ ከያዝን በኋላ መቆየት እንፈጋለን ስንላቸው ይሰመለኛል፤ 139 ናቸው። አሥራ አምስታችንን ደበደቡን። በጣም ነው የጎዱን።”

ሌሌች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ቢኖሩም እርሳቸው ግን ብዙ እንዳልተጎዳ የሃምሳ አልቃ ለአከ ወልዳይ ገልጿዋል።

“መሳሪያችንን ቀምተው ያለ ምንም ሥራ ተቀምጠን ነበር እምንውለው” ያሉት አምሳ አለቃ ወልዳይ፣ ከዚህ ቀደም ወደ ሀገራቸው የተመለሱ የትግራይ ተወላጆች ታስረው ይገኛሉ ብለዋል።

ከአሁን በፊት የተመለሰን አንድ አባል አስረውታል። ገንዘባቸውን አልሰጧቸውም። የት እንዳሉም የማይታወቅ ሰዎችም አሉ። አንድ ትግራዋይ የሰለም አስከባሪ ተመልሶ ወደ ቤቱ የሄ የለም። በየቦታው ነው አስርዋቸው የሚገኙት።"

መጀመሪያ ላይ ሁርሶ የሚባል ማሰለጠኛ ላይ አስርዋቸው ነበር። እሁን ግን ሰብስበው የት እንደወሰዱዋቸው አይታወቅም። ስልካቸውም አይሰራም ይላሉ። የህወሃት ታጋይ የነበሩትና በጡረታ ተሰናብተው ከሰላም አስከባሪዎች ጋር ምግብ ቤት ውስጥ ይሰሩ እንደነበር የገለጹት ብረይ ታደሰ ወደ አውሮፕላን ማረፍያው እንደገቡ በድንገት በጥፊና በርግጫ አንደተመቱ ገልጸዋል።

በሰላም ጥበቃ ሥራ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ደቡብ ሱዳን ቀሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:26 0:00

“ወደዚህ እንደገባን በድንገት መጥተው መሬት ላይ ጥለው መቱኝ። የነበረኝን ንብረት ቀምተውኛል። ሻንጣየ የሞባይል ስልኬን ሁሉንም ንብረቴ መታወቂዬን ሳይቅር ነው የወሰዱብኝ። እዛ የነበረች ሰራተኛ ገላግላኝ ነው ወደ ውስጥ የገባሁት።”

ስቪል ሰራተኛ በመሆቸው ወደ ሃገርቸው ለመመልስ ወደ አውሮፕላን ማረፍያው እንደሄዱና “በትግራይ ተወላጅነቴ” ያሉት ያሉት ድብደባ ከደረሰባቸ በኋላ ግን ለህይወቴ አስጊ በመሆኑ ልመመለስ አልፈለኩም ብለዋል።

ሻምበል ሕሉፍ የተባሉ ወታደራዊ መኮነን በበኩላቸው ሁኔታውን አስቀድሜ ስለተረዳሁት ቀድሜ ወጥቻለሁ ብለዋል። ለመሆኑ የስጋታችሁ ምክንያት ምንድነው ለሚለው ጥያቄ፣

“ስጋታችንማ ተጋሩን እምታጠፋ ሃገር ሆናለች። ከሌሎች ሃይሎች ተባብረው ተጋሩን እየጨፈጨፉ ነው። ይህኮ በግልፅ የሚታይ ዓለም እሚያውቀው ነገር ነው። ስለዚህ እንደኛ ከሰላም ማስከበር የተመለሱ እየታሰሩ እያየን እኛ እሰሩን፣ግደሉን ብለን ልንሄድላቸው ነው? ይህ ነው ስጋታችን። አንሄድም ብለን ቀርተናል።”

ይህ ሁሉ ግርግርና ድብደባ ተፈጸመ የተባለው፣ በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በሚገኘው ጁባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ መሆኑ ተገልጿል። የአውሮፕላን ማረፍያው የአቪየሽን ደህንነት ጥበቃ ሃላፊ ጂቶ ሚሎ እዛ ውስጥ ስለተፈጠረው ክስተት አብራርተዋል።

ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ደቡብ ሱዳን ሲመጡ፣ ለተባበሩት መንግውውታት የሰላም ጥበቃ ውውራ ነው ያሉት ሚሎ፣ ያንድ ሃገር ሰዎች ናቸው መንግሥት ወደ ሃገራቸው ሊመልሳቸው ፈልጎ፣ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮች ግን መመለስ አንፈልግም ብለዋል ሲሉ ገልጸዋል።

“ወደ አውሮፕላን ማረፊያው መጡ። እርስ በራሳቸው መደባደብ ጀመሩ። የመንግሥት የሆኑ ሰዎች የትግራይ ተወላጆቹን እየለዩ እጠቅዋቸው። ከዛ 15ሰዎች ጥበቃ እንዲያደርጉላቸው ለተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት/ዩኤንኤችሲአር/ እጃቸውን ሰጡ። የተቀሩት ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ጉዛቸውን ቀጠሉ”ብለዋል።

XS
SM
MD
LG